የሀዛን መግለጫ ! የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከዚህ ዓለም በሞት መለየትን በተመለከተ

የሀዛን መግለጫ ! የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከዚህ ዓለም በሞት መለየትን በተመለከተ

ኦሮሞ ነጻነት ግንባር, ሚያዚያ 19, 2011

adda ummataከኣንጋፋዎቹ ታጋይና ፖለቲከኛ የኦሮሞ ተወላጆች መካካል ኣንዱ የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በዛሬዋ ዕለት (ሚያዝያ 19, 2011) ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉን የሰማነዉ በከፍተኛ የሀዘን ስሜት ነዉ። የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ርዕሰ-ብሔር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በህይወት ዘመናቸዉ ለኦሮሞ ነጻነት በተደረገዉ የትግል ተሳትፎ ጉልህ ሚና ከነበራቸዉ ግለሰቦች ዉስጥ ኣንዱ ናቸዉ። ዶ/ር ነጋሶ በኢትዮጵያም ሆነ በኦሮሞ ፖለቲካ ዉስጥ በተለያዩ ወቅቶች በተለያዩና ባመኑባቸዉ መንገዶች ተሰልፎ የሕዝቦች ነጻነትና ሰብኣዊ መብቶች እንድረጋገጡ፣ እንድሁም እዉነተኛ ዴሞክራስያዊ ስርዓት በሀገሪቷ እንድሰፍን ሰፊ እንቅስቃሴ ኣድርጓል።

ዶ/ር ነጋሶ ባሁኑ ጊዜ በሕዝቦች ትግል በኢትዮጵያ ፖለቲካ የታየዉን የለዉጥ ጅማሮን ተከትሎ በኦሮሞ ነጻነት ግንባርና በኢትዮጵያ መንግስት መካካል እርቅና ስምምነት እንድፈጠር በማግባባቱ ሂደት የሸምጋይነት ሚናቸዉን ለመጫወት ከፍተኛ ጥረት ስያደርጉ ከነበሩት ቅን ኣሳቢ ዜጎች መካካልም ኣንዱ ነበሩ። በኦሮሞ የነጻነት ትግል ጎራም ሆነ በኣጠቃላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ ጉልህ ሚና የነበራቸዉ ዶ/ር ነጋሶ፣ በሀገሪቷ ፖለቲካ እንደሳቸዉ ያሉ በሕብረተሰቡ መካካል መረዳዳት፣ መቻቻልና እርቅን ለማስገኘት ተስፋ የሚጣልባቸዉ ዜጎች በሚፈለጉባት በዚህች ወሳኝ ወቅት ላይ ከጎናችን መለየታቸዉ ታላቅ ሀዛን ነዉ።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማዉን ከፍተኛ ሀዛን እየገለጸ ለመላ ቤተሰቦቻቸዉና ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉ እንድሁም እሳቸዉን ድንገት ከጎኑ ላጣዉ ሕብረተሰብ ሁሉ መጽናናቱን ይመኛል።

ድል ለኦሮሞ ሕዝብ !

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
ሚያዚያ 19, 2011