የምርጫ ቦርድ የኦነግ ጠቅላላ ጉባኤን አስመልክቶ አስተላልፎ የነበረውን ውሳኔ አሳድሶታል

 

የምርጫ ቦርድ የኦነግ ጠቅላላ ጉባኤን አስመልክቶ አስተላልፎ የነበረውን ውሳኔ አሳድሶታል

የኦነግ መግለጫ – መጋቢት 28/2022

የምርጫ ቦርድ ተወካዮች ለአንድ አመት በቤት ውስጥ እስር ላይ የነበሩትን የድርጅቱን ሊ/መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳን መጎብኘቱን አስመልክቶ ኦነግ በቀን 16/03/2022 መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በተጨማሪም የምርጫ ቦርድ በ24/02/2022 ጠቅላላ ጉባኤን እና ሌሎች ጉዳዮችን አስመልክቶ ያስተላለፋቸውን ውሳኔ ኦነግ እንደደረሰዉ ማሳወቅ እንወዳለን።

ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ እነዚህን አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን ያስተላለፈው የኦነግ መሪዎች ያስገቡትን ቅሬታዎች እና የፍርድ ቤት ውሳኔን ተከትሎ እንደሆነ አሳውቆናል።ይሁን እንጂ ኦነግ በዚሁ ጉዳይ ላይ ከአንድ አመት በፊት ተመሳሳይ ውሳኔ ተላልፎ መቀበላችንን አሳውቀን ነበር። የአሁኑ ውሳኔ ጥቅት መሻሻሎች ቢደረጉበትም ከአምናው ውሳኔ ጋር አንድ መሆኑን ተገንዝበናል።

ኦነግ በህገወጥ መንገድ የተዘጉበት ጽ/ቤቶቹ እንዲከፈቱ ፣ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ የታሰሩ አባላቶቹ ይፈቱ ዘንድ በተደጋጋሚ የምርጫ ቦርድን ሲጠይቅ ነበር። እንዲሁም የድርጅቱ ሊ/መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከቁም እስር ተለቀው እንደ ዜጋ መንቀሳቀስ እንዲችሉ እና የድርጅቱንም ተግባራት እንደ ማንኛውም ህጋዊ ፓርቲ መከወን እንዲችሉ ጭምር ስናመለክት ነበር። በተጨማሪም ያለ አግባብ በህገወጥ መንገድ በገዥው ፓርቲ የጸጥታ ሀይሎች የተዘረፉት የድርጅቱ ንብረቶች ማለትም ኮምፒውተሮች፣ የእጅ ስልኮች፣ሰነዶች እና ተሽከርካሪዎች እንዲመለሱልን በተደጋጋሚ ስናመለክት መቆየታችን ይታወሳል።

የምርጫ ቦርዱ በአሁኑ ጊዜ እየወሰደ ያለውን ውሳኔ እና እርምጃዎችን ኦነግ እያደነቀ አፈጻጸሞቹ ግልጽነት ባለው መልኩ እና ከኦነግ ጋር በመነጋገር እንደሚተገበሩ ተስፋ እናደርጋለን። ከድርጅቱ እና ከድርጅቱ ሊ/መንበርር እውቅና ውጭ በኦነግ ስም የሚሰሩም ሆነ የሚደረጉት የሚድያ ዘመቻ ተቀባይነት እንደሌላቸው አጥብቀን እናስገነዝባለን። ግለሰብም ሆነ የትኛውም ተቋም በዳውድ ኢብሳ ከሚመራው ኦነግ እውቅና ሳያገኙ ማንንም በኦነግ ስም ማስተናገድ ህገ ወጥነትን ማበረታታት ነው። በተጨማሪም የሚድያ ተቋማት ተጨባጭ እውነታን ከማዛባት እና ነገሮችን ከማባባስ እንዲቆጠቡ እናሳስባለን። ከኦነግ ጋር መስራት የሚፈልግ የትኛው ተቋም ሆነ ሚድያ ህጋዊ እና ትክክለኛውን የግንኝነት አካሔድ ተከትሎ መስራት እንዳለበት ጭምር ማስገንዘብ እንወዳለን።

የምርጫ ቦርድ ሀኔታዎችን በቅርበት እንዲከታተል እና ውሳኔዎቹ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላትን ጭምር በማሳተፍ ህጋዊ እና ቅደም ተከተሉን በጠበቀ መልኩ እንዲተገበሩ እንዲያደርግ ማስታወስ እንወዳለን። የምርጫ ቦርድ ተጨማሪ ጫና በማድረግ የድርጅታችን አባላት እና አመራሮች እንድያስፈታ፣ የተዘጉ ጽ/ቤቶቻችን እንዲያስከፍት እና አሁንም አባላቶቻችንን እና ደጋፊዎቻችንን እያሳደዱ ማሰር እንዲያስቆም አንጠይቃለን።

በመጨረሻም የኦሮሞ የፖሌቲካ መሪዎችን ለማስፈታት እና የኦነግን ድርጅታዊ ተቋምን ለመጠበቅ ያለመታከት ለፈትህ የታገሉ የኦሮሞ ህዝብ፣ የኦሮሚያ ዜጎች እና የኢትዮጵያ ህዝቦችን ማመስገን እንወዳለን።የኢትዮጵያ ህዝቦች እና የአለም አቀፍ ተቋማት በሃገሪቱ የተከሰተውን የፖለቲካ ቀውስ ለመፍታት በትብብር እንዲሰሩ እና ፍትሐዊ የፖለትካ ውይይት በኢትጵያ ውስጥ እንዲካሔድ እንዲሁም ለነጻነት እና አካታች ዲሞክራሲ መረጋገጥ የበኩላችሁን እንኑድትወጡ እንጠይቃለን።

 

ድል ለሰፊው ሕዝብ

የኦርሞ ነጻነት ግንባር

መጋቢት 28/2022

ፊንፊኔ