የኦነግ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ባቴ ኡርጌሳና ሹፌራቸው ወጣት ወንድወሰን አብዱልቃድር መታሰር አስመልክቶ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር መግለጫ
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆነዉ አቶ ባቴ ኡርጌሳና ሹፌራቸው ወጣት ወንድወሰን አብዱልቃድር መጋቢት 20/ 2021 በኦሮምያ ልዩ ዞን ፊንፊኔ ዙሪያ ቡራዮ ፖሊስ ጣብያ ተይዘው መታሰራቸውን የኦነግ መገንዘብ ችሏል።
አቶ ባቴ ኡርጌሳ ያለምንም ጥፋት እና ወንጀል የታሰሩትን የኦነግ አመራርና ጓዶቹን በተደጋጋሚ ሂዶ ሲጠይቃቸው እንደነበረና በዚሁ እለት ጓዶቹን ለመጠየቅ በሄደበት በቡራዮ ፖሊስ ጣብያ መታስራቸውን ነው የተረዳነው። እንደማንኛውም የእስርኞቹ ቤተስብ እና ጓደኞቻቸዉን እንደሚጠይቁ ሁሉ አቶ ባቴም የሥራ ባልደረቦቹን ለመጠየቅ በሄዱበት ያለ አንዳች ጥፋት ከመስሪያ ቤት መኪና አሽከርካሪያቸው ወጣት ወንድወሰን አብዱልቃድር ጋር ፖሊስ ምንም አይነት የህግ አግባብ በሌለው ይዞ ያሰራቸው ሲሆን አቶ ባቴ እንደማንኛውም ዜጋ የታሰሩ ጓዶቹን የመጠየቅ መብት እንዳለው እናምናለን ።
ስለዚህ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አቶ ባቴ ኡርጌሳ፥ ሹፌራቸውና በተለያዩ ማጎሪያ ጣቢያዎች ታስረው ያሉ የኦነግ የፖለቲካ እስረኞች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ በአፅንኦት ይጠይቃል
በመጨረሻም መሰል ድርጊት በተለያዩ ቦታዎች በስፋት እየተደረገ ስለሆነ ከሃገሪቱ ህግ በሚጻረር ያለ አንዳች ጥፋትና ህጋዊ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ የኦሮሞያ ዜጎች እስር በአስቼኳይ እንዲቆም እናሳስባለን ።
ድል ለሰፊው ህዝብ
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
መጋቢት 21/2021
ፊንፊኔ