ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር የምርጫ ቦርድ የቦርዱ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ለሚድያ ተቋማት የስጠችውን መግለጫ በተመለከተ የተስጠ ወቅታዊ አቋም
ጥር 2021 ዓም
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር እንደ ተፎካካሪ ሀገራዊ ፖለቲካ ፖርቲ ከምርጫ ቦርድ የምንጠብቀው ቢያንስ በገለልተኝነት ሀላፊነቱን እንደወጣ ነው። ይሁን እንጂ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ የምርጫ ቦርዱየኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ተወካይ በሚዲያ በቀረበች ቁጥር እውነት እና ሀቅን ለማዛበት የምትስጣቸው ኦነግን የተመለከቱ አስተያየቶች የገለልተኝነት መርህን የጣሱ መሆናቸውን እየተገነዘብን እንገኛለን።
በቅርቡ ከአሜሪካ ድምፅ አማሪኛ ፕሮግራም(በVOA ) ጋር በደረገችው ቃለምልልስ ሁለት በገሃድ የሚታዩ ትርክቶችን አዛብታ አቅርባለች፣ ለቦርዱም አመራር የሚደርሱት መረጃዎች እንዲህ የተዛቡ እና ቦርዱ ያለምንም ጭብጥ እና ከመረጃ ውጭ በዚህ ሁኔታ የሚገነዘቡ ከሆነ እጅግ በጣም ያሳስበናል። በዚሁ መስረት በድርጅቱ ውስጥ ያገጠሙትን የሃሳብ ልዩነት ተብየዉ በተመለከተ፣
1ኛ ” ሁለቱ ወገን ያስተላለፉት ህገወጥ እገዳ ነው ጣልቃ እንድንገባ ያስገደደን።”
2ኛ “የስነምግባር እና ቁጥጥር ኮሚቴያቸውም አለመግባባቱ ን መፍታት አለመቻሉን ገልፆልናል።” የማለት ቃል በቃልም ይሁን ይህን ይዘት ያለው አስተያየት ነው ለ VOA የተናገረችዉ። የተቋሙ የህዝብ ግንኙነት ትክክለኛውን እውነታ ባላማከለ መልኩ በዚህ ደረጃ የተሳሳተ መረጃ ማስገንዘብ የተቋሙን ክብር እና መልካም ሥነ ምግባር የሚያጎድፍ ሥራ ላይ የተስማራች በመሆኑ ከዚህ ድርጊት እንድትቆጠብ ከወድሁ እንመክራለን።
በተስጠው ቃለ ምልልስ መስረትም የመጀመሪያው ህገወጥ እገዳ የተባለው ቦርዱ በደብዳቤ ጠይቆን ያቀረብነውን ቃለ ጉባኤ ሳይመለከቱ እና በቃለ ጉባዔው የተካተቱትን ውሳኔዎች ያላዳስስ ሆኖ አግኝተናል ። ይህ ደግሞ ተገቢ አለመሆኑ ግልፅ ነው። በሽኝ ደብዳቤ ተደግፎ ለምርጫ ቦርዱ ፅ/ቤት ተልኳል ያለውን ደብዳቤ ለውሳኔ ሰጭ አካል ማቅረብ ያልቻለው አካል ኦነግን ህገወጥ እገዳ አድረክ ብሎ አስተያየት መስጠት ሀቅን ማዛባት ብቻ ሳይሆን ታማኝነት ማጉደል ጭምር መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን ።
ህገወጥ እገዳ በሁለቱም ወገን ተፈፅሞም ቢሆን ቦርዱ የቀረበለትን ውሳኔ ከድርጅቱ ህገ ደንብ አንፃር መርምሮ ውሳኔውን መቀበል ወይም ውድቅ አድርጎ በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት እንዲያደርጉት አቅጣጫ መስጠት እንጂ ጣልቃ የሚያስገባ ምንም ዓይነት ሕጋዊ መስረት አልነበረም። በሁለቱም ወገን የቀረበው ውሳኔን ማሳወቅ እንጂ አቤቱታም አልነበረም። በምርጫ ቦርድ አዋጅ መሠረት ደግሞ ቦርዱ ጣልቃ የሚገበው በሁለቱም ወገን አቤቱታ ሲቀርብለት ብቻ ነው። ከሁለቱ ወገን የቀረቡ ጣልቃ የመግባት ጥያቀዎች እስካልቀረቡ ድረስ ሕገ ወጥ እና አዋጅን የሚፃረሩ መሆናቸውን ማስንገዘብ እንፈልጋለን.
በእኛ እምነት በተከታታይም ለብዙ ግዜያት ለቦርዱ እደገለፅነው፣ ይህ ችግር በድርጅቱ የህግ ማዕቀፍ ውስጥ መፈታት ያለበት የውስጥ ጉዳይ ነው። በመተዳደሪያ ደንባችንም በግልፅ የተደነገገ የግጭት አፈታት ሥነሥርዓት፣ እርከኖች እና ስልጣን የተሰጠቸው አካል በግልፅ ተቀምጦ ያለ ለዘመናት ድርጅታችን ስንጠቀምበት የከረመ መሆኑ ግልፅ ነው።
በተጨማሪም የድርጅቱ ህገ ደንብ ተሟጦ ሳይተገበር ( “The principle of exhaustion ) በድርጅቱ ውስጥ ስልጣን ባለው አካል ሳይታይ ወደ ሦስተኛ ወገን እንዲደርስ ህገደንባችን አይፈቅድም የሚል ፅኑ አቋም አለን።
ስለዚህ ይህን ጉዳይ በተመለከተ በበኩላችን የቦርዱን ዳኝነት በማሸት ወይም ጣልቃ ገብነት በመጠየቅ ያስገባን አቤቱታ አልነበረም። እንደ ሕጋዊ አዋጁ የምርጫ ቦርዱ በሕግ እንደገለልተኛ ተቋም የሚጠበቅበትን እና የጠየቅነውን ብቻ ቢያደርግ ያስመሰግነዋል፤ መሆንም ያለበት እንደዛ ነበር። ይልቁንስ የአባሎቻችን በህገወጥ ሁኔታ በየቦታው መገደል መታሰር እና የቢሮዎቻችን ያለ ህግ መዘጋት በተመለከተ በሕግ የተስጣቸውን ቢያስፈጽሙ እስየው በተባለ ነበር ለምናቀርብ ጥያቀ እዛ ግባ የማይባል መልስ ሲስጡ ከርመዋል።
በተጨማሪም “የስነምግባር እና ቁጥጥር ኮሚቴ አለመግባባቱን በተመለከተ መፍታት አንችልም “ብለው ለቦርዱ ያስገቡት ሪፖርት አለ የተባለውንም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ምንም ከዚህ ጋር ተዛማችነት ያላቸውን ርፓርት በፍጹም አለቀረብንም መፍታት አንችልምም ተብሎ የተገለፀ የለም ። ይህን ለማረጋገጥ ደግሞ የድርጅቱ ስነምግባር ኮሚቴ በሕይወት እስካሉ ድረስ ማረጋገጥ ቦርዱን የሚሳነው ነው ብለን አናምንም። በዚህ ደረጀ የተሣሣተ መረጃ ለብዙሃን መገናኛ መስጠት ደግሞ የቦርዱን ስም እና የተቋቋመለትን ድርጅታዊ እንድምታ አይመጥንም። በአስቸኳይ መታረም እንዳለበትም በጥብቅ እንጠይቃለን። ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ የቦርዱ ሕዝብ ግንኙነት ሆነ ብለው ይኸን ሀቅ አዛብቷዋል። የድርጅቱ የስነምግባር ቁጥጥር ኮሚቴ ጉዳዩን መርምረው የደረሱበትን የውሳኔ ሀሳብ በጥቅሉ ለሚመለከታቸው ሕጋዊ አካል እና ለሕዝብ ጭምር ይፋ አድርጓል። ድርጅታችንም ለቦርዱም ይህን ሀቅ የውሳኔውን ጥቅል ሀሳብ ወደ አማርኛ አስተርጉመን በሸኚ ደብዳቤ አሳውቀናል። ቦርዱ የኮሚቴውን አባላት በፅ/ቤቱ ጠርቶ ባነጋገረበት ወቅትም ውሳኔ መስጠት አንችልም ብለው መልስ አልስጡም ፤ የሐምሌ 19 እና 20/2012 ስብሰባ ህገወጥ እንደነበረና ያን ተከትለው የተፈፀሙት ሂደቶች በሙሉ ህገወጥ መሆነቸውን በግልፅ ቋንቋ ነው የተናገሩት። ዝርዝር የውሳኔ ሀሳቡን ግን በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት ለሚመለከተው የድርጅቱ ውሳኔ ሰጭ አካል እንጂ ለቦርዱ ሪፖርት ማድረግ በድርጅቱ የውስጥ ድንጋጌ መስረት የማይፈቅድላቸው መሆኑን ነበር የተናገሩት። ይሆን እንጅ ይህን ውሳኔ ሐሳብ ከድርጅቱ ማጣራት ስቻል ይህን ሀቅ አጣሞ ማቅረብ ህዝባዊ ሀላፊነትን በሚገባ አለመወጣት ብቻ ሳይሆን ሆነ ብለው የግልን አድሎአዊ አቋም በተቋም ስም ለማራመድ መሆኑ ታውቆ ተጠያቅነት መኖር አለበት እያልን በመጨረሻም ድርጅታችን ኦነግ እነዝህ ተገዳሮቶች በዚህ ተጠያቂነት በጎደለው ሁኔታ የሚቀጥሉ ከሆነ ግን፣በበኩላችን እኛም በየጊዜው ለቦርዱ የሚንፅፈቸውን ደብዳቤዎች እና መርጃዎች ለህዝብ ግልፅ ለማድረግ እንገደዳለን።
ስለዚህ ምርጫ ቦርዱ በአዋጅ የተስጠውን የሕግ አግባብ ገለልተኝ በመሆን እንድወጣ እያሳስብን አሁንም ደግመን ችግሮቹን ለመፈታት የድርጅቱን የውስጥ ህግ ማቀፊን መከተል ተገቢ መሆኑን እንገልጻለን።
ድል ለስፊው ሕዝብ
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
ጥር 02/2021 ዓም