በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሔደ ያለው ተከታታይ የንጹሃን ዜጎች ፍጅት ለህግ እና ስርአት መፍረስ ጉልህ ማሳያ ነው።

 

በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሔደ ያለው ተከታታይ የንጹሃን ዜጎች ፍጅት ለህግ እና ስርአት መፍረስ ጉልህ ማሳያ ነው።

የኦነግ መግለጫ

የብልጽግና መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ ከ2018 ዓ/ም ጀምሮ በጅምላ የተገደሉት የኦሮሞ ቁጥር እና ሌሎች ሰላማዊ ሰዎች እጅጉን ከፍተኛ ነው። ሰሞኑን በመላው ኦሮሚያ በታቀደ መልኩ አየተካሔደ ያለው የንጹሃን ዜጎች ጭፍጨፋ፣ ህጻናትን ጨምሮ የብዙ ሰቶች እና አረጋውያንን ህይወት ቀጥፏል።የጥቃቱ መጠን እና የሚጨፈጨፉት ዜጎች ቀጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።ይህ ፍጅት እጅግ አሳሳቢ እና በ1880ዎቹ በሚኒሊክ 2ኛ ወረራ 5 ሚልየን የኦሮሞ ህዝብ መጨረስን ጨምሮ ያለርህራሔ ከተካሔደው እግር ፣እጅ እና ጡት እቆረጣ እና ጋር ይመሳሰላል። በአሁኑ ጊዜ የዶ/ር አብይ አመራር ያንን የቀድሞ አሃዳዊ የኢምፓየሪቱን ስርአት እና አገዛዝ ለመመለስ ያለመታከት እየሰራ መሆኑን እያየን ነው።ያንን የቅኝ አገዛዝ ስርዓት በማደስ ለመመለስ እና በጭቁን ህዝቦች ላይ ለመጫን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንቅስቃሴዎች እየተጀመሩ ይገኛል። በግልጽ እየታየ እንዳለው በብልጽግና መንግስት የ1880ዎቹ የቅኝ ግዛት ወረራ እራሱን እየደገመ ይገኛል።የዚህ አመላካች ደግሞ “የሚንሊክ ዘመቻ” ተብሎ ሰሞኑን በተጀመረው እንቅስቃሴ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ማለትም ወሎ፣ሸዋ፣ ወለጋ እና በትግራይም ጭምር ዜጎች በጭካኔ ተጨፍጭፈዋል።የብልጽግና መንግስት ያንን የቅኝ አገዛዝ ዘመን እምፓየር የነበረችዋን ኢትዮጵያ በጠበንጃ ጉልበት ፣ በ”አንድ የሰው” የበላይነት እና የአንድ ፓርቲ አገዛዝ ስር “መደመር”በሚል ሀሳብ መልሶ ለማምጣት ሲተጋ ማየት ያሳዝናል።

ምንም እንኳን ከዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን መምጣት በኋላ የአሀዳዊ ስርአት ግንባታ መካሄድን ማየት እና የኦሮሞ ግድያዎችን መስማት የተለመደ ቢሆንሞ በተለይ ሰሞኑን በህዳር 30/2021 እና ታህሳስ 1/2021 በፈንታሌ ወረዳ ምስራቅ ሸዋ፥ ኦሮሚያ ወስጥ በንጹሃን የከረዩ ኦሮሞ ላይ በተካሔደው የጅምላ ጭፍጨፋ እጅግ አዝነናል።ይህ ጭፍጨፋ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ሆን ተብሎ ታስቦበት እና ታቅዶበት ህዝቡን ለመደምሰስ የተካሔደ አረመኔያዊ ተግባር ነው። በ30/11/2021 የብልጽግና መንግስት የቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ ወጣቶች እነሱን ባለመደገፋቸው ብቻ እንድታሰሩ ትዛዝ አስተላልፎ ነበር። ነገር ግን ወጣቶቹን ማግኘት ስላልቻሉ ቤተሰቦቻቸውን እየደበደቡ ኢ-ሰብአዊ በሆነ መልኩ መሬት ላይ እየጎተቱ እስርቤት ለመውሰድ አስገደዷቸው።የአካባቢው ነዋሪዎችም ይህንን ኢ-ሰብአዊ ድርጊታቸውን በማየት ታጣቂዎቹ ቤተሰቦችን ከማስገደድ ይልቅ ችግሩን በመነጋገር በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ይጠይቃሉ። ቀጥሎም ችግሮችን በባህላዊ መንገድ በሽምግልና ለመፍታት የአካባቢው ሽማግሌዎች በ1/12/2021 ተሰብስበው ነበር።ነገር ግን የጸጥታ ሀይሎች ለእርቅ በተሰበሰቡ የአካባቢ ሽማግሌዎች ላይ ተኩስ በመክፈት አባ ገዳ እና አባ ቦኩ(የአካባቢው የተከበሩ ሽማግሌዎችን) ጨምርሮ 13 ሰዎችን ገደሉ።በ ጭፍጨፋ መካሔድ የተደናገጡት የአካባቢው ማህበረሰብም ብሶታቸውን ለመግለጽ ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣሉ። የሚያሳዝነው የጸጥታ ሃይሎች በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ አሁንም ተኩስ በመክፈት ሌላ 50 ንጹሃን ሰዎችን በመግደል የሟቾች ቁጥር ወደ 63 ከፍ አለ። የቆሰሉት እና በጅምላ ታፍሰው የታሰሩት ዜጎች ቁጥር ስፍር የለውም።

እነዚህ ግድያዎች በንጹሃን እና ከግጭቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት በሌላቸው ሰዎች ላይ በመከናወኑ በደፈናው የዘር ፍጂት ተግባር ተፈጽሟል። የተረሸኑት ሀሉ ኑሮዋቸውን ለማሸነፍ የሚጥሩ ንጹሃን ዜጎች ናቸው።ጭፍጨፋው ከተካሄደባቸው መካከል ድጋፍ የሚፈልጉ አዛውንቶች ፣ህጻናት ምንም አይነት ተቃውሞ ላይ የልተሳተፉ ሴቶች ይገኙበታል። በአካል ይዘው ለህግ ማቅረብ እየቻሉ የብልጽግና መንግስት የጅምላ ጭፍጨፋውን መምረጡና ያልታሰበ እልቂት በንጽኋን ላይ ማስከተሉ እጅግ አሳዝኖናል። የብልጽግና መንግስት እንዲህ አይነት በጭካኔ የተሞላ አረመኔያዊ ተግባሮችን ለዜጎች ርህራሄ በሌለው እና ሀላፊነት በጎደለው አኳኋን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጭፍጨፋ እያካሄደ ይገኛል።

በተመሳሳይ መልኩ የብልጽግና መንግስት ሰው አልባ የጦር አውሮፕላን/ድሮን/ በመጠቀም በወሎ ኦሮሞ ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ አድርሷል።በዛሬው እለት ጠዋት የወሎ ከተሞች ከሚሴንና ባቲን በቦምብ በመደብደብ ንጹሃን ዜጎችን በጀምላ ገድሏል።የብልጽግና መንግስት በዜጎች ላይ የሚያካሂደውን በጭካኔ የተምላ ጨፍጨፋ ኦነግ በአጅጉ ያወግዛል።ይህ በንጹሃን ላይ የሚካሔደው የጅምላ ጭፍጨፋ ያለፈውን የህዝቦችን ቁስል ከማገርሸት አልፎ ሀገሪቱን ወደ ባሰ ትርምስ የሚከታት ተግባር ነው።

የብልጽግና ገዥው ቡድን በአብዛኛው የኦሮሚያ አካባቢዎች ላይ ሰፊ የጦርነት ዘመቻዎችን በማካሔድ በንጽኋን ላይ ጥቃት እያደረሰ ይገኛል።የብልጽግና መንግስት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ለፈጸመው የዘር ፍጂት እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ተግባሩ ሀላፊነት መውሰድ እንዳለበት እና ተጠያቅም እንደሚሆን ማስገንዘብ እንወዳለን።እነዚህ ድርጊቶቹ የሀገርቱን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ከማባባስ በዘለለ ፋይዳ እንደሌላቸውም ጭምር ማሳሰብ እንወዳለን።የአለማቀፍ ማህበረሰብም ይህንን ድርጊት እንዲያወግዝ እያሳሰብን በተለይም የብልጽግና ገዥ ቡድን በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን የሰባዊ መብት ጥሰቶችን እንዲመረምር እንጠይቃለን።በተለይም የአለማቀፍ የሰባዊ መብት ኮሚሽን/IHRC/,የተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ም/ቤት(UNSC),የአፍሪካ ህብረት /AU/ የሰላም እና ደህንነት አካል እና የአለም መሪዎች ንጹሃን የኦሮሞ እና የኢትዮጵያን ህዝብ የአለማቀፍ ህግ እና ድንጋጌዎች በሚጠይቁት ልክ ከለላ እንድታደርጉላቸው እንጠይቃለን።

ባጠቃላይ የብልጽግና ገዥ ቡድን የአብሲንያን የግዛት ማስፋፋት ድብቅ ፓሊሲ እና የአሀዳዊ አገዛዝን በጭቁን የኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ ያለፍላጎታቸው ለመጫን ጥረት እያደረገ መሆኑ አስገራሚ እና አሳዛኝ ነው።

በመሆኑም፥

1. የፋንታሌን ጭፍጨፋ በእጅጉ እናወግዛለን፤ጉዳዩ በገለልተኛ አካል ተጣርቶ አጥፊዎቹ ለህግ እንዲቀርቡ እንዲደረግ ጥሪ እናደርጋለን።በተጨማሪም በኦሮሚያ ለይ የታወጀውን ጦርነት በእጅጉ እያወገዝን ገዥው ቡድን ከድሪጊቱ እንዲቆጠብም ጭምር እናስጠነቅቃለን።

2. የብልጽግና ገዥ ቡድን የዘር ፍጂት እና የግዛት ማስፋፋት ዘመቻዎችን በተቀናጀ መልኩ በአብዛኛው የኦሮሚያ አካባቢዎች እያካሔደ ስለሆነ የኦሮሞ ህዝብ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አጥብቀን እናስጠነቅቃለን። የኦሮሞ ህዝብ እና ሌሎች ጭቁን ህዝቦች በዚህ በ21ኛው ክ/ዘመን የ1880ዎቹን የቅኝ ግዛት ማስፋፋት ለመቀበል ዝግጁ አይደሉም።አንድ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረውን ተከታታይ ወረራ እና የግዛት ማስፋፋት አባዜ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም ከመቸውም ጊዜ በላይ በአንድነትን መቆም አለብህ።በተለይም በቀየህ እና በመሬትህ ለይ የሚፈጸምብህን የጅምላ ጭፍጨፋ ለመከላከል በንቃት መዘጋጀት አለብህ። የብልጽግና ቡድን መሪዎችህን፣ ታላላቆችን እና ጠንካራ ግለሰቦችን በማሰር እና በመግደል ተቋሞችህን አፍርሶ ለሌላ የክፍለ ዘመን ባርነት ሊዳርግህ እየተዘጋጀ ስለሆነ ጥንቃቄ እንድታደርግ እናሳስባለን።ተቋማትህን፣ መሪዎችህንና ጠንካራ ግለሰቦችህን የመከላከል እና የክልልህን ሰላም እና ጸጥታ የመጠበቅ ግዴታ አለብህ።

3. መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች የትኛውንም በገዥው ቡድን የሚደረገውን ብሔር ተኮር የንጹሃን ጭፍጨፋ እስራት እና እንግልቶች በህዝቦች መካከል ግጭትን የሚያባብሱ እና ሀገርን የሚያፈርሱ በመሆናቸው እንድታወግዙ ጥሪ እናስተላልፋለን።በተጨማሪም የተወሰኑ የኢትዮጵያ ምሁራን እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የግዛት ማስፋፋት እና የቅኝ ገዥነት አባዜ የተጠናወታችሁ አጉል ህልማችሁን ለማሳካት በህዝቦች መካከል ጥላቻን ከመዝራት እና ከጠባጫሪነታችሁ ተግባር እንድትቆጠቡ ጥሪ እናደርጋለን።ይልቁን አካታች እና ህብረ ብሔራዊ የሆነ ፌደራል ሪፐብልክ የሽግግር መንግስትን መልሶ ለማቋቋም እና የፓለቲካ ውይይትን ለማካሔድ በሀቀኝነት ተሳትፋችሁ የበኩላችሁን ድርሻ አንድትወጡ ጥሪ እናደርጋለን።

4. የአለማቀፉ ማህበረሰብ ሚዛናዊ እና ፍትሀዊ በሆነ መልኩ የተፋላሚ ወገኖችን ባህሪ በማወቅ ሁሉንም ያቀፈ የሀገሪቱን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የሚፈታ አውነተኛ ድርድር እንዲካሔድ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ እናስተላልፋለን።

በመጨረሻም ሁሉም የፖለቲካ ተዋናዮች እና ባለድርሻ አካላት ከራስ ተኮር ፍላጎት ወጥተው ለኢትዮጵያ ህዝቦች ሰላም ፣ፍትህ እና እኩልነት መረጋገጥ በአንድነት እንድትሰሩ ጥሪ እናደርጋለን።

ድል ለሰፈሐው ህዝብ!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር

ታህሳስ 3, 2021