በወሎ ኦሮሞ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የብልጽግና ፓርቲ እና የአማራ ክልል መንግስት ወረራ አስመልክቶ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መግለጫ

 

በወሎ ኦሮሞ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የብልጽግና ፓርቲ እና የአማራ ክልል መንግስት ወረራ አስመልክቶ የኦሮሞ ነጻነት
ግንባር መግለጫ
የኦነግ መግለጫ- ሚያዝያ 21, 2022
ኦነግ በዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የብልፅግና ፓርቲ መንግስት በ‹ዳግማዊ ምኒልክ ሪቫይቫል ርዕዮተ ዓለም እና ፕሮጀክት›
እየተመራ ነው ብሎ ያምናል። ይህም የጨቋኝ ቡድኖችን የግዛት ማስፋፋት ማበረታታት እና የሌሎች የኢትዮጵያ ጭቁን ብሔር
ብሔረሰቦች ዳር ድንበር ማፍረስ እና መጠቅለልን ያካትታል።በዚህ አጥፊ አስተሳሰብ የብልፅግና ፓርቲ መንግስት በጭቁን
ህዝቦች ውስጥ ያለውን ከነሱ ጋር የሀሳብ ልዩነትያላቸውን በማጥፋት የገዢውን ቡድን የግዛት ማስፋፋት ስራ ላይ ይገኛል። በዚህ
ሂደት አብዛኛው የአማራ አዋሳኝ ብሄሮች ብሄረሰቦች እንደ ኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ትግራይ ክልል መንግስታት ተጎጂ
ናቸው። በተለይም የኦሮሚያ ክልል ከበርካታ አቅጣጫዎች ከሰሜን፣ምስራቅ እና ምዕራብ ጥቃት እየተፈፀመ ሲሆን በነዚህ
በመንግስት በሚደገፉ የተስፋፊ ቡድኖች በየጊዜው ይወረራል። አብዛኛዎቹ የክልል ሚሊሻዎች የብልጽግና ፓርቲ-ተዛማጅ የክልል
መንግስታት እና የኤርትራ ጦር ላለፉት ሶስት አመታት ተኩል በዚህ አውዳሚ ጦርነት ውስጥ ያለማቋረጥ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ከመጣ ካለፉት ሶስት አመት ተኩል ጀምሮ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጦርነት እና ስልታዊ ግድያ እና ግዛት
የማስፋፋት ዘመቻዎች ቢደረጉም አሁን በዋሎ ኦሮሞ ሰላማዊ ዜጎች ላይ እየተካሄድደ ያለዉ ግድያ እና መፈናቀል ግን እጅግ
አሳዛኝ ነው። በአሁኑ ወቅት የአማራ ክልል ከማዕከላዊ መንግስት ጋር በመተባበር በዋሎ ኦሮሞ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ሰፊ ጦርነት
እያካሄደ ይገኛል። በአሁኑ ጊዜ የዋሎ ኦሮሞ ንፁሀን ህጻናትና አዛውንቶች በመንግስት በሚደገፉ የአማራ ሚሊሻዎች በሚባሉ
አሸባሪ ቡድኖች እና በአማራ ፋኖ እና በተባባሪ ቡድኖች ጥቃት እየተፈፀመባቸው ይገኛል። በዋሎ ኦሮሞ ሰላማዊ ዜጎች ላይ
የሚፈጸመው ግድያ ያለ ለዩነት ዘር ማጽዳትን ኢላማ ያደረገ ጥቃት ከመሆኑም በተጨማሪ ንብረታቸውን በማቃጠል እና
በማውደም፣ በመዝረፍ፣ ሰላማዊ አርሶ አደሮችን ከመሬታቸው ለመንቀል ያለመ ነው።
ይህ ጥቃት በረመዳን ጾም መባባሱ ደግሞ በስልጣን ላይ ያለዉ ቡድን በወሎ ኦሮሞ ላይ ያለውንጭካኔና አስከፊ ዓላማ ያሳያል።
ገዥው ቡድን አብዛኛው የዋሎ ኦሮሞን የሙስሊም ሀይማኖት እየናደ እና እየፆሙ የሚገኙትን ንፁሀን ዜጎች እየገደለ ነው። ይህ
ተግባር የኢትዮጵያ ኢምፓየር የተገነባበትን መርህ ማለትም አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ሀገር የሚለውን መርህም
እየተተገበረ መሆኑን ያሳያል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ገዥ ቡድን በሌሎች የኦሮሚያ ክልሎች ከ80,000 በላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት፣
የሪፐብሊካን ጋርድ፣ የኤርትራ ጦር፣ የአማራ ሚሊሻዎች እና የአማራ ፋኖ አሸባሪ ቡድን በማሰማራት ጦርነቱን በህዝባችን ላይ
የጀመረውን ጦርነት አጠናክሮ ቀጥሏል። ጦር ሰራዊቱ የኦሮሞ ልጆችን እና ቤተሰቦችን ከመሬቱ ለማፈናቀል በታቀደው የጥላቻ
ጦርነት የዜጎችን ንብረቶች፤ ሰዎቹን ከመኖሪያ ቤታቸው ጋር፣ ከብት፣ እህል እና ሰብል ሳይቀር እያቃጠሉ ይገኛሉ። ስለዚህ ኦነግ
ይህን የጥቃት እርምጃ አጥብቆ ያወግዛል
እናም፥
1. እነዚህ ወራሪ ሃይሎች ከወሎ ክልል በአስቸኳይ እንዲወጡ ጥሪ ያደርጋል። እነዚህን አሸባሪ ቡድኖች አደራጅቶ
ያሰማራው በዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የብልጽግና መንግስት በወሎ ለደረሰው ግድያና ውድመት ተጠያቂ
መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን። ኦነግ በህዝቦች መካከል የሚነሱ ግጭቶች መስፋፋት በኢትዮጵያ ህዝቦች ሰላም፣
ደህንነት እና አብሮ መኖር ላይ ከፍተኛ መዘዝ እንዳለው እና ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ክፉኛ እንደሚጎዳ በድጋሚ ሊገልጽ
ይወዳል።
2. አማራ ታጣቂ ቡድኖች፣ የአማራ ክልል መንግስት በተለይም የአማራ ኤሊቶች ከነሱ የመስፋፋት አላማ እንዲታቀቡ
ጥሪ እናደርጋለን። በተለይም የአማራ ሚሊሻዎች እና ፋኖዎች ይህ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችን ህይወት
የጎዳውን የግዛት ማስፋፋት ህልማቸዉን እንዲያቆሙ እና የአማራን ህዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና
ህዝቦች ጋር ያላቸዉን ሰላማዊ መስተጋብር እያቃወስ ካለው ተግባራቸው እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን።
3. የኤርትራ የውጭ ወታደሮች ከኦሮሚያ እንዲወጡ በድጋሚ እንጠይቃለን። እንዲሁም ይህ የኤርትራ መንግስት
ተግባር በኦሮሚያ እና በኤርትራ መካከል ያለውን የወደፊት ግንኙነት እንደሚጎዳ አዉቆ የኤርትራ ህዝብ
መንግስታቸው የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እንዲያወግዝ እንጠይቃለን።
4. በትህምክተኛው ቡድን የግዛት ማስፋፋት ዘመቻ ውስጥ የተሳተፉት የጭቁን ብሄሮች እና ብሄረሰቦች ሚሊሻዎች በዚህ
ግጭት ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያቆሙ ጥሪ እናደረጋለን። በተለይም የአፋር ታጣቂዎች፣ የሶማሌ ሚሊሻዎች
እና የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ታጣቂዎች በዚህ ዘመቻ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እንድያቆሙእናሳስባለን። በዚህ ከቀጠለ
ሊከተል ለሚችለው ያልተፈለገ ውጤት የእነዚህ ክልሎች መንግስታት ኃላፊነቱን ይወስዳሉ።
በመጨረሻም የወሎ ኦሮሞ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በህብረት እንድትቆም፣ ቤትህን፣ ቤተሰባችሁን እና ንብረቶቻችሁን
ከአጥቂዎች እንድትከላከሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። በሌላ በኩል በአገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የምትገኙ ሰፊው
የኦሮሞ ማህበረሰብ እና የኦሮሚያ ተወላጆች ከወሎ ወንድምና እህቶቻችሁ ጋር እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
በተቻለው መንገድ ሁሉ የኦሮሞ ህዝብ እና የኦሮሚያ ዜጎች ከውሎ ኦሮሞ ጋር በአንድነት እንድትቆሙ እናሳስባለን።
በውጪ የምትገኙ የኦሮሞ ተወላጆች ለወሎ ኦሮሞ ድምፅ በመሆን እና ድጋፍ በማሰባሰብ በወሎ ክልል ላሉ ወንድምና
እህቶቻችሁ እንድትደርሱላቸው እንጠይቃለን።
አሁንም፣ አለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በኢትዮጵያ ገዥ ቡድን ላይ ጫና እንዲያደርጉ
እና በከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣ ፤ በሰው ህይወት እና በሀገሪቱ ውድመት በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚደረገው ጦርነት
እንዲቆም እንጠይቃለን።
ድል ለሰፊው ህዝብ!
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር/ኦነግ
ሚያዝያ 21 ቀን 2022