ለኦነግ ቀርቧል ስለተባለው ግልፅ ያልሆነ የስብሰባ ጥሪ መረጃው የለንም።
(የኦነግ መግለጫ -ጥቅምት 29,2020)
ነገ ጥቅምት 30,2020ዓም ለሚካሄደው ስብሰባ ለኦነግ ጥሪ ቀርቧል መባሉን በተመለከተ ድርጅታችን ኦነግ
የተደረገለት የስብሰባ ጥሪ ኣለመኖሩንና ኣንዳችም መረጃ ያልደርሰው መሆኑን ለአባሎቻችን እና ለመላው
ህዝባችን እንገልፃለን።
የተወሰኑ የኦሮሞ የሃገር ሽማግሌዎች በአካል ተገኝተው ነገ አርብ ሊካሄድ ነው ለሚባለው ስብሰባ ለኦነግ ጥሪ
መደረጉን አስመልክቶ እኛን በመጠየቃቸው ለመላው ህዝብ ተጨባጭ መረጃ ይደርስ ዘንድ ይህንን መግለጫ
ለማውጣት ተገደናል።
ኦነግን ጨምሮ ሌሎችንም የፖለቲካ ድርጅቶችና የሃገር ሽማግሌዎች እንደሚሳተፉበት በተገለጸው በዚህ
ስብሰባ ላይ እንዲካፈል ለኦነግ ጥሪ መደረጉን እና እንደሚሳተፍም እየተወራ መሆኑን ከነሱ ለመረዳት የቻልን
ሲሆን፡ ድርጅታችን ስለስብሰባው የሚያውቀው ነገር እንደሌለና እንዲሳተፍም የተደረገለት ጥሪ አለመኖሩን
ያስታውቃል።
የህዝባችን መብት እንዲከበር የማይፈልጉ የትግላችን እንቅፋት የሆኑ አካላት እና ቡድኖች ህዝባዊው
ተቃውሞና ትግል ሲያስጨንቃቸው ሊቃውንትና ሸማግሌዎችን እንደመሳሪያ ተጠቅመው በማወናበድ
በህዝብ ላይ የባርነት እድሜያቸውን ማስረዘምን ሁሌም እንደስልት መጠቀም ባህላቸው ነው።
የኦሮሚያ ዜጎች እያጋጠማቸው ላለው አለመረጋጋት እና ከባድ የደህንነት ስጋት ዘላቂ መፍትሄ ለማስገኘት
እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ጊዜ ኦነግ ያልሰማውን ጉዳይ እንደተነገረው አድርገው ለማቅረብ መሞከር የህዝብ
ድጋፍ ማጣታቸውን በግልፅ ያሳያል። በተጨማሪም ለውስብስቡ ችግሮች የመፍትሄ ሃሳብ በማቅረብ የትግል
ኣመራር በመስጠት ላይ የሚገኙትን እንደኦነግ ያሉ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶችን እንዲሁም የተከበሩ
ሊቃውንቶች እና ሸማግሌዎችን በሚባለው መድረክ ላይ በማቅረብ በተሳሳተ ፕሮፓጋንዳ ሊነጉዱባቸው ነው
ብለን እናምናለን።
ይህ አይነት አካሄድ የአገሪቱን ዜጎች አንቆ ለያዘውና የህዝብን ደህንነት በበለጠ ወደከፋ አሳሳቢ ሁኔታ
እየወሰደ ላለው ችግር መፍትሄ ይሆን ዘንድ ለቀረበውና በህዝብም ከፍተኛ ምተቀባይነት ያገኘውን በሳል
የመፍትሄ ሃሳብ መልስ በመስጠት የሽግግር መንግስት ምስረትን ከመደገፍ ይልቅ፡ በተለያየ ድራማ
ውዥንብር በመፍጠር እውነታን አድበስብሰው በህዝብ ጫንቃ ላይ ለመቆየት መገላታቱ ትልቅ ኪሳራ ነው።
በድጋሚ በአባ ገዳዎች እና በሽማግሌዎች ይገኙበታል በሚባለውና ኦነግም እንደተጋበዘ ስለሚነገረው ግልጽ
ያልሆነ ስብሰባ ምንም መረጃ እንደሌለን ለሁሉም እየገለፅን ላለው ችግር ዘላቂ መፍትሄ የሚሆነው ኦነግ
ላቀረበው የኦሮሚያ ብሄራዊ ሽግግር መንግስት ጥሪ በጎ ምላሽ በመስጠት ሽግግሩን እውን ማድረግ እንደሆነ
እናሳስባለን።
ድል ለሰፊው ህዝብ!
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
ጥቅምት 29, 2020ዓም