የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ካህናት ግደያን አስመልክቶ ጉዳዩ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ የተሰጠ የኦነግ መግለጫ
በዚሀ ሳምንት ማገባደጃ ላይ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዝቋላ አቡነ ገብሬ መንፌስ ቅዱስ ገዳም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (EOTC) አራት ካህናት እንደታፈኑበት እና ከዚያ በኋላ መገደላቸውን ባሰጣዉ መግለጫ ሰምተናል። ኢኦተ ቤ/ን ዜናውን ያረጋገጠ ሲሆን፣ የህይማኖት ተቋሙ ልሳን የሆነው የቴሌቭዥን ጣቢያም ‹‹ሼኔ›› ብሎ የጠራውን ቡድን በመክሰስ ዝግቧል።
የኦሮሚያ በሄራዊ ክለላዊ መንግስት “ሰላምና ፀጥታ ቢሮ” ዜናውን አረጋግጦ ድርጊቱን የፈጸመዉ ‘ሸኔ’ የሚባል የታጠቀ ቡድን ነው በማለት ወቅሷል።
ኦነግ በንጹሃንና ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸመውን ማንኛውንም ዓይነት ግድያ ፣ እንዲሁም በንጹሃን ሰላማዊ ዜጎች ፣ ታዋቂ ሰዎች ፣ በሃይማኖት መሪዎች ፣ በሴቶች ፣ በወንዶች ፣ በወጣቶች ወይም በአረጋውያን ላይ የሚፈጸሙ ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥቃቶችን ያወግዛል ። ኦነግ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈፀሙ ግድያዎችእና የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች በሁሉም መልኩ መወገዝ እንዳለባቸው ያምናል።
በሁሉም ደረጃ ላይ የሚገኙ የመንግስት መዋቅሮች የሁሉንም ዜጎች ህይወትና ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባቸውም አጽንኦት ሊሰጠው ይገባል ብለን እናምናለን። ጥፋትን በሌላ አካል ማላከክና ማጭበርበር ባለፉት አምስት ዓመታት የመንግስት የእለት ተግባሩ ቢሆንም ለዜጎች ግን ምንም አይነት ውጤት አላመጣም።
ኦነግ በበኩሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በሀገሪቱ ውስጥ የሃይማኖትና የሞራል ሃላፊነቱን የሚወጣበትን አግባብ እና ሚና በድጋሚ መገምገም እንዳለበትእንደገና ያሳስባል።አንዳንድ አባላቱና መሪዎቹ በትግራይ ጦርነት ወቅት ሁኔታውን ከማቃለል እና መፍተሄ ከመሆን ይልቅ ግጭቱን ለማቀጣጠል የበኩላቸውን ድርሻ ተጫዉተዋል፡፡በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተፈጸመውን አሰቃቂ የአየርና የሰው አልባ አውሮፕላን ድብደባ እና የጅምላ ግድያ ቤተክርስቲያኒቱ ይህን አረመኔያዊ ድርጊት ከማውገዝ ተቆጥባለች ወይም መርጣ ተናግራለች። ድብቅ አጀንዳቸው ሲነካ
Email: olfheadoffice@gmail.com www.oromoliberationfront.org
ብቻ መርጦ መናገር ከትዮጵያ ዕርቶዶክስ ተዋህዶ ቢተክርስቲያን የሚጠበቅ የሞራላዊ ድርጊት አይደለም። በመሆኑም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በሀገሪቱ እየተከሰቱ ባሉ ግጭቶችና ሁከቶች ውስጥ እንደ ሰላም ፈጣሪ አካል የምትጫወተውን ሚና እንደገና እንድታጤነው እናሳስባለን። ቤተ ክርስቲያን እንደ ሃይማኖታዊ ተቋም እጆቿን ከፖለቲካ እንድታስወጣና እንዲሁም በስልጣን ላይ ባለው ገዥ አካል እና በተቃዋሚዎቹ መካከል በሚከሰተዉ ግጭት ዉስጥ ከመግባት መቆጠብ አለባት ብለን በጽኑ እናምናለን።
ኦነግ በተደጋጋሚ እንደሚለዉ ሁሉ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀመው የዘፈቀደ ግድያ እና ሌሎችም በገለልተኛ አካል እና በገለልተኝነት እንዲጣራ ይጠይቃል። ከላይ እንደተገለጸው በነዚህ ካህናት ላይ ለተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ ኃላፊነት መውሰድ ያለበት የክልል እና የፌደራል መንግስት እና የየራሳቸው መዋቅር ነው። መንግስት እንደዚህ አይነት የወንጀል ድርጊቶችን በመወቃቀስ እና በመሸፋፈን ማለፉን አቁሞ በምርመራ እንዲጣራ ጉዳዩን ለገለልተኛ አካል ክፍት ማድረግ አለበት። መንግስት በስህተትም የሁን እያወቀ ‘ሸኔ’ እያለ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትም በተመሳሳይ ለሚደረገው ገለልተኛ ምርመራ መተባበር አለበት።
ድል ለሰፊው ሕዝብ
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
የካቲት 25/2024
ፊንፊኔ