የብልፅግና ፓርቲ መንግስት የፖለቲካ እስረኞችን እና ቤተሰቦቻቸውን በአካልና በሥነ-ልቦና ማሰቃየት ማቆም አለበት

 

የብልፅግና ፓርቲ መንግስት የፖለቲካ እስረኞችን እና ቤተሰቦቻቸውን በአካልና በሥነ-ልቦና ማሰቃየት ማቆም አለበት

 

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መግለጫ

በብልጽግና ፓርቲ (PP) የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት በተለይ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (OLF) አባላትና ደጋፊዎች ላይ የፖለቲካ ጫናና አፈና ማካሄዱን ቀጥሏል። የፒፒ የደህንነት መስሪያ ቤት ምንም አይነት ተገቢ የፍርድ ቤት የችሎት ሂደት ሳይካሄድ በህገ ወጥ መንገድ በማሰር እና በእስር ቤቶች ውስጥ በማስቀመጥ ከፍተኛ የኦነግ መሪዎችን እና አባላትን እያሰቃየ ይገኛል። እስረኞቹ በተለያዩ የፖሊስ ጣቢያዎችና እስር ቤቶች ከቤተሰቦቻቸውና ከዘመዶቻቸው ርቀው እንዲቆዩ ተደርጓል።

የብልጽግና መንግስት በእስረኞች ላይ የሚፈፀመዉ ጥሰት በተለያዩ ማቆያዎች ይፈፀማል። የቡራዩ እስር ቤት እስረኞች በአግባቡ ከማይያዙባቸውና የሚንገላቱበት ጣቢያዎች አንዱ ነው። እነዚህን መጥፎ ሁኔታዎች በመቃወም ትናንትና ከገላን እስር ቤት ወደ ቡራዩ ከተላለፉት ከፍተኛ የኦነግ መሪዎች የምግብ አድማ ሲያደርጉ ቆይተዋል። አቶ ሚካኤል ቦረን፣ ኬኔሳ አያና፣ ዳዊት አብዴታ፣ ሌሚ ቤኛ፣ ገዳ ገቢሳ እና በቴ ኡርጌሳ ለተወሰነ ጊዜ ምግብ ካቆሙ መካከል ይገኙበታል። በዚህም ምክንያት የእነዚህ ከፍተኛ አመራሮች ጤንነትና አጠቃላይ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ደህንነት በየቀኑ እየትጎዳ ነው። የእነዚህ አባላት ቤተሰቦች እነርሱን እንዳይጠይቋቸው ይከለከላሉ አልፎም ተደጋጋሚ ትንኮሳ ይደርስባቸዋል።

ኮሎኔል ገመቹ አያና የፍርድ ቤት ቀጠሮዎችን ለረዥም ጊዜ ሲከታተሉ ቆይቷል። ኮሎኔል ገሜቹ አያና ትናንት ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ዘግቶ ከእስር መፈታት ሲገባው አሁንም በሜክሲኮ ፖሊስ ማረሚያ ቤት ይሰቃያል።

በብልጽግና መንግሥት እስር ቤት ከቆዩት በርካታ ከፍተኛ የኦነግ አመራሮችና አባላት መካከል 30 ያህሉ በሰበታ ፖሊስ ጣቢያ ታስረዋል።በቅርብ ጊዜ ወዲህ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከእነዚህ የፖለቲካ እስረኞች መካከል አያሌዎቹ ምግብ፣ ውሃና ሌሎች መሰረታዊ ሰብዓዊ ፍላጎቶች እያጡ ነው። አቶ ደቻሳ ወርቁ፣ ጋዜጠኛ ቢቂላ አመኑ እና ጋዜጠኛ ደሱ ዱላ ምግብ እንዲቀርብላቸው ከማይፈቀድላቸው መካከል ይገኙበታል።የሰበታ ፖሊስ ጣቢያ ኃላጥበቃ ሃላፊ ሳጂን ደጀኔ ከበደ ቤተሰቦችና ዘመዶች ለታሳሪዎቹ ወደ ጣቢያው የሚያመጡትን ምግብ ደፍተዉ ማበላሸታቸው ተዘግቧል። እነዚህ በህገ ወጥ መንገድ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎችና አመራሮች ሊደረግላቸዉ የሚገባዉን መሰረታዊ የሰው ፍላጎት ይበልጥ የተነፈጉ መሆናቸው ብልጽግና ፓርቲ መንግስት ለቤተሰብ፣ ለዘመድ፣ ለኦነግ እና ለኦሮሞ ህዝብ ያልዉን ጥላቻ የሚያሳይ ነው።

የብልጽግና መንግሥት በዜጎች ላይ የፈጸመውን አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዚህ መልኩ እያየን መምጣታችን የሚያሳዝን ነው። በተቃራኒው ደግሞ የብልጽግና መንግሥት እንዲህ ላለው አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይሁንታ እያገኘ ያለ ይመስላል። ይህን የፕሬስ መግለጫ በሚወጣበት ጊዜ በመላው ኦሮሚያ በሚገኙ ስፍር ቁጥር በሌላቸው የብልጽግና መንግስት ማቆያ ማእከላት ውስጥ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ የኦነግ መሪዎችና አባላት አካላዊ፣ ስነ ልቦናዊና የጤና ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል።እነዚህ መሪዎችና ቤተሰቦቻቸውም ለፖለቲካዊ አመለካከታቸው ሲሉ ብቻ በብልጽግና መንግሥት እንዲህ ያለ ሥቃይ እየደረሰባቸው ነው። ሁኔታው በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ሌሎች ክልላዊ ግዛቶችም ቢሆን ከዚህ የተለየ አይደለም። በመሆኑም ኦነግ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በተለይም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከነዚህ የፖለቲካ እስረኞች ጋር እንዲቆሙና ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ጥሪውን ያቀርባል። በተጨማሪም የኦሮሞ ህዝብ ለእነዚህ መሪዎች ደህንነት ትኩረት ሰጥቶ ከነሱና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በአንድነት እንዲቆም ጥሪ ያችንን እናቀርባለን።

 

ድል ለሰፊው ህዝብ!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር

የካቲት 10 ቀን 2022 ዓ.ም

ፊንፊኔ