ኢትዮጵያ አሁን ከገባችበት አጣብቅኝ ሁኔታ ለመውጣትና መፍትሄውን በሚመለከት
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦ.ነ.ግ) መግለጫ
ሚያዝያ 28-2021
ምንም እንኳን የኢትዮጵያ የሽግግር ሂደት መልካም ፈጻሜ እንዲኖረው በአብዛኞቹ ፖሌትካ ፓርቲዎች፣አለም አቀፍ ማህበረሰብ፣ ታዛቢዎች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጂቶች ያላሳለሰ ጥረት ቢደረግም ሁኔታዎች ሀሉ መስመር ስተው ሀገሪቱ በአሁኑ ሰዓት የመፍረስ እድሏ ከፍተኛ እንደ ሆነ ሀሉም ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛል።
እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች ጅምላ ግድያ እና ከፍተኛ የዜጎች መፈናቀልን አስከትሏል። የመንግስት ታጣቂዎች/ሚሊሻዎች ከቁጥጥር ውጭ በመሆናቸው የተነሳ ንጹሃንን መግደል እና ሴቶችን መድፈር የተለመደ ተግባራቸው ሆኗል። የአማራ ሚሊሻ እና የኤሪትሪያ ታጣቅዎች በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ማለትም ወሎ ፣እና ትግራይ እንዲሁም በምዕራብ ኦሮሚያ ቤ/ጉሙዝ ላይ እየፈጸሙ ያሉት ነውጥ እና በደል ለተጎጂዎች ሰብአዊ እርዳታ እንኳን ማድረስ በማይቻልበት ሁኔታ ላይ ደርሷል። እነዚህ እንደ ማሳያነት የተጠቀሱ እንጂ ሀኔታዎቹ ከዚህ በከፋ እየተባባሱ መሆኑ ሀቅ ነው።
የጋራ ፌዴራላዊ ሀገር እንደ መሆኗ እና እንደ ባለድርሻ አካል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር/ኦነግ/ ችግሮቹ ከመባባሳቸው አስቀድሞ የተለያዩ የመፍትሔ ሀሳቦች እና መውጫ አማራጮችን ቢያቀርብም ሰሚ ጆሮ ያለው የሚመለከተው አካል ስላልነበር ዛሬ ሀገሪቱ ውጥንቅጥ ውስጥ ገብታ እያየን እንገኛለን።
ችግሮችን ለመቀልበስ እና ብሎም ውጤታማ ሰላማዊ ሽግግር እንዲኖር የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከትብብር ለህብረ ብሄር ፈደራሊዝም(ትህብፌ) ጋር በመሆን በሚያዝያ 2012 ሰፋ ያለ ሀሳቦችን የያዘ ሰነድ አቅርቦ ነበር።ሃሳቡም መንግስት በህገ መንግስቱ ማዕቀፍ ውስጥ የሆነ እና ወደ ሁሉን አቀፍ ሰላማዊ ሽግግር እንድያመራ የሚመክር ነበር።
የኛ ምክረ ሃሳብ በውስጥም በውጭም ችግር የገጠመው ሪፎርም እንዴት መመራት እንዳለበት፤የሚመለከታቸውን ባለ ድርሻ አካላት በማሳተፍ እና መግባባትን በመፍጠር ፖለቲካውን ማረጋጋት እና እንዴት በሂደት በህገ-መንግስቱ ማዕቀፍ ውስጥ የተረጋጋ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር መፈጠር እንዳለበት በግልጽ የሚጠቁም ነበር። ይሁን እንጂ ያቀረብነው የመፍትሔ ሀሳብ በገዥው ፓርቲ ተቀባይነት ሊያገኝ አልቻለም።
በድጋሚ በመስከረም 13-2020 ኦነግ በግልጽ በወጣ መግለጫ መንግስት በትብብሩ አባላት የተሰጡትን የመፍትሔ ምክረ ሀሳቦችን እንደገና እንዲያጤነው ፣ ብሎም ህግ እና ስርዓትን በተከተለ መልኩ የኢትዮጵያን ህዝቦች የቆየ ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ እንዲያደርግ እና ትብብሩም አብሮት ለመስራት ፈቃደኛ መሆኑን በመግለጽ ጠይቆት ነበር።ነገር ግን ገዠው ፓርቲ አሁንም ምክረ ሀሳቡን ውድቅ በማድረግ በተቃራኒው ዜጎችን በተለይ ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ደጋፊዎች እና አባላትን ማሳደድ፣ማሰር፣ማስጨነቅ እና በጭካኔ የተሞላ ዘግናኝ ግድያዎችን ማካሔዱን ቀጠለበት። በተለይ አፈናው እና ግድያው በኦሮሞ ነጻነት ግንባር/ኦነግ/አባላት ላይ እየተባባሰ በመሆኑ በዝያው መግለጫ አቤቱታችንን ለአፍሪካ ህብረት፣ለአውሮፓ ህብረት፣ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ም/ቤት እና ለተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በማስገባት ጉዳዩን በትኩረት አይተው ኢትዮጽያን ከህገ-መንግስታዊ ቀውስ እና ብጥብጥ ለመታደግ ጥብቅ እርምጃ እንዲወስዱ ጭምር ጠይቀናል።
በታህሳስ 12-2020 ኦነግ ባወጣው መግለጫ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት የተወሳሰቡ የፖለቲካ ሁኔታዎችን በመዘርዘር መፍትሄ ሊበጅላቸው እንደሚገባ አስጠንቅቆ ነበር። በመግለጫውም የክልሎች የመንግስት መዋቅሮች ፈርሰው ባሉበት፣ግጭት እና ጦርነት በተባባሰበት እና አለመረጋጋት በመላው ሀገሪቱ ላይ በሰፈነበት ሁኔታ ምርጫ ማካሄድ እንደማይቻል ገልጸን ነበር። በመሆኑም ከሚፈጠረው የፖለቲካ አለመረጋጋት እና የደህንነት ስጋት ራስን ለማዳን ብሎም ፖለቲካዊ ምክክር እና መግባባት
ለመፍጠር በኢፌድሪ ማዕቀፍ ውስጥ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የራሱን የኦሮሚያ ብሄራዊ የሽግግር መንግስት ለማቋቋም መዘጋጀት እንዳለበት ለህዝቡ አመላክተናል።
በሚያዝያ 07- 2021 ለአለም ማህበረሰብ ባሰራጨነው የዉስጥ ሜሞ የውጪ ሀይሎች እና የአማራ ሚሊሻ በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በመግባት ዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን እና ይህ ካልቆመ የሀገሪቱ ብሎም የአፍሪካ ቀንድ የደህንነት ጉዳይ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ አሳስበናል።
እንደ አለመታደል ሆኖ ገዥው ቡድን ያቀረብናቸውን ገንቢ ሀሳቦች ወደ ጎን በመተው አማራጭ የፓሌትካ ሀሳቦች ላይ በሮችን ዘጋ። በዚህም ሳይበቃ ንጹሃንን ማፈን፣ የጸጥታ ሀይሎችን በመጠቀም ተቃዋሚ ፖርቲዎችን ማሸበር እና ማሰሩን ተያያዘው። የሚፈጸምባቸውን የመብት ጥሰት በመቃወም የሚሰሙትን ድምጾች ለማፈን ህገወጥ ገደቦችን መጣል እና ወታደራዊ አገዛዝን እንደ መሳርያ መጠቀምን የዘወትር ተግባሩ አደረገ። በአሁኑ ጊዜ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ወሎን ጨምሮ አብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል በወታደራዊ አገዛዝ ስር ወድቀው ይገኛሉ።
እጅግ አሳዛኙ ደግሞ የሀገሪቱን 40% የሚሆነውን የኦሮሞ ብሔር የወከሉትን አነግ እና ኦፌኮን ከምርጫ ሂደቱ ተገፍተው እንዲወጡ ከማድረግ አልፎ በሀገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ላይ ተሳትፎ እንዳይኖራቸው ተደርጓል።
በማጠቃለያም በአሁኑ ጊዜ የሀገሪቱ የደህንነት ሀኔታ እና የፓለቲካ አለመረጋጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መሆኑ እጅግ አሳስቦናል። ሁኔታዎች መገመት በማይቻልበት ፈጥነት እየተባባሱ ለከፍተኛ ስርዓት አልበኝነት መንገስ በር ከፍቷል።
ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያሳተፈ ሀለንተናዊ የፖለቲካ ወይይት ካልተካሔደ፤መሪዎቻቸውን ጨምሮ የፖሌቲካ እስረኞች ካልተፈቱ፤አወዛጋቢውና ወዳቂ የሆነውን የምርጫ ህደት በድጋሚ እንዲታይ ካልተደረገ በሀገሪቱ የነገሰው ጽንፈኝነት እና ውጥረት በመባባስ ወደ ለየለት ስርዓት አልበኝነት እና ደም መቃባት ሊያመራ ይችላል ብለን እናምናለን።
ችግሮችን ለማቃለል የአለማቀፍ ማህበረሰብ እያከናወነ ስላለው ተግባራት እያመሰገንን ከጉዳዩ አሳሳቢነት የተነሳ አሁንም ተጨማሪ ስራ እንደሚጠበቅባችሁ እና ችግሮቹ ሁለንተናዊ መፍትሔ አስክያገኙ ጭምር የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ ጭምር ማስገንዘብ እንወዳለን።
በመሆኑም የአፍሪካ ህብረት/አሕ/፣ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ም/ቤት(የተመ) ፥ የአውሮፓ ህብረት /ኢዩ) እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ኦነግ ያቀረበውን ሀሳብ በአጽኖት በመቀበል ገዥው በድን ወታደራዊ ዘመቻውን በማቆም ወደ ባሰ ጥፋት አያመራ ካለው አካሄዱ ተመልሶ መፍትሔ ሊያመጣ ወደሚችለው ውይይት እንዲመለስ ጫና እንድታደርጉ ኦነግ ይጠይቃል።
ሀሌም እንደምንለው ውስብስብ ለሆነው የኢትዮጵያ ፓለቲካ ዘላቂና አስተማማኝ መፍትሄ የሚገኘው አካታች የሆነ የዲሞክራሲ ህደት መፈጠር እና ሀሉንም ተወካይ የፖለቲካ ሀይሎችን ያሳተፈ የፖለቲካ ምክክር ሲኖሮ ቢቻ እንደሆነ ኦነግ በጽኑ ያምናል።
በመጨረሻም አነግ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ለመስራት፤ ለፓለቲካ ውይይቶች ሁኔታዎችን ለማመቻቸት እና የፖለቲካ አቋም ልዩነቶችን በሰላማዊ አኮኋን መፍታት እና እና የጋራ መግባባቶችን በመፈጠር መጻኢ እጣ ፈንታ በመወሰን ላይ ጽኑ አቋም እንዳለው በአጽኖት መግለጽ እንወዳለን።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር/ኦነግ/
ሚያዝያ 28-2021
ፊንፊኔ/አዲስ አበባ