የእንኳን ደስ ኣላችሁ መልዕክት ለሲዳማ ሕዝብ !

የእንኳን ደስ ኣላችሁ መልዕክት ለሲዳማ ሕዝብ !

(ኦነግ – ኅዳር 13, 2012 ዓ.ም.)

የሲዳማ ሕዝብ ለብቻዉ ክልላዊ መንግስትን (Regional Government) መመሥረት ኣልያም ባለፉት 24 ዓመታት ከሌሎች የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋራ ተዳብሎ በአንድ ክልላዊ መንግስት (የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት) ሥር ስተዳደር በቆዬ መልኩ መቀጠል ከሚሉት ሁለት አማራጮች መካከል ያሻዉን ለመምረጥ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብቱን ተጠቅሞ የራሱን ነፃ ድምጽ በመስጠት ለመወሰን መብቃቱ የሕዝቡ የረዥም ዓመታት የነፃነት ተጋድሎ ዉጤትና የድል ፍሬ ነዉ። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በአጠቃላይ ለሰፊዉ የሲዳማ ሕዝብ፣ በተለይ ደግሞ የሕዝቡን ትግል ዛሬ ለተገኘዉ የድል ምዕራፍ ለማብቃት አስተዋጽዖ ላበረከቱት የሲዳማ ሕዝብ ታጋይ ልጆች ሁሉ እንኳን ደስ ኣላችሁ ! ስንል በከፍተኛ የደስታ ስሜት ጭምር ነዉ።

ከዚህር ምጫ ዉጤት (Result) እንደ ትልቅ ስኬትና ድል መታየትም ሆነ ልበረታታ፣ እንዲሁም ትምህርት ልቀሰምበት የሚገባዉ ብለን የሚንለዉ ሕዝቡ ያለምንም ተጽዕኖና ፍርሃት ነፃ ሆኖ ከቀረቡለት ሁለት (2) አማራጮች መካከል የልቡን/ ያሻዉን መምረጥ/መወሰን መቻሉ ነዉ። በመሆኑም፣ ከላይ እስከ ታች ያሉትን የመንግስት መዋቅሮችን ጨምሮ ይህንን ምርጫ በማሳካቱ ሂደት ዉስጥ የበኩላቸዉን ድርሻ የተወጡት አካላትና ግለ-ሰቦች ሁሉም ምስጋናና የእንኳን ደስ ኣላችሁ መልዕክት ይገባቸዋል እንላለን።

ከዚህ የሲዳማ ሕዝብ የምርጫ ሂደት የተገኘዉ ተሞክሮ ((Experience) ዛሬም ድረስ በኢትዮጵያ የቀዉስ ምንጭና የደህንነት ስጋት፣ እንዲሁም የዕድገት ጠንቅ ሆኖ ላለዉ ፖለቲካዊ ችግር ዘላቂና መሠረታዊ መፍትሄ ለማስገኘት ትምህርት ይሆናል ወይም ያግዛል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
በድጋሜ ለሰፊዉ የሲዳማ ሕዝብና ይህንን የምርጫ ሂደት ለማሳካት ሲጥሩ ለቆዩት ሁሉ እንኳን ልፋታችሁ ልፍሬ በቃ ! እንኳን ተሳካላችሁ ! እንኳን ደስ ኣላችሁ ! እንላለን።

ድል ለሰፊዉ ሕዝብ !

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር
ኅዳር 13, 2012 ዓ.ም.