ከኦነግ ዜና በአማርኛ – Adda Bilisummaa Oromoo

ኢትዮጵያ አሁን ከገባችበት አጣብቅኝ ሁኔታ ለመውጣትና መፍትሄውን በሚመለከት
ኢትዮጵያ አሁን ከገባችበት አጣብቅኝ ሁኔታ ለመውጣትና መፍትሄውን በሚመለከት

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦ.ነ.ግ) መግለጫ

ሚያዝያ 28-2021

ምንም እንኳን የኢትዮጵያ የሽግግር ሂደት መልካም ፈጻሜ እንዲኖረው በአብዛኞቹ ፖሌትካ ፓርቲዎች፣አለም አቀፍ ማህበረሰብ፣ ታዛቢዎች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጂቶች ያላሳለሰ ጥረት ቢደረግም ሁኔታዎች ሀሉ መስመር ስተው ሀገሪቱ በአሁኑ ሰዓት የመፍረስ እድሏ ከፍተኛ እንደ ሆነ ሀሉም ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛል።

እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች ጅምላ ግድያ እና ከፍተኛ የዜጎች መፈናቀልን አስከትሏል። የመንግስት ታጣቂዎች/ሚሊሻዎች ከቁጥጥር ውጭ በመሆናቸው የተነሳ ንጹሃንን መግደል እና ሴቶችን መድፈር የተለመደ ተግባራቸው ሆኗል። የአማራ ሚሊሻ እና የኤሪትሪያ ታጣቅዎች በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ማለትም ወሎ ፣እና ትግራይ እንዲሁም በምዕራብ ኦሮሚያ ቤ/ጉሙዝ ላይ እየፈጸሙ ያሉት ነውጥ እና በደል ለተጎጂዎች ሰብአዊ እርዳታ እንኳን ማድረስ በማይቻልበት ሁኔታ ላይ ደርሷል። እነዚህ እንደ ማሳያነት የተጠቀሱ እንጂ ሀኔታዎቹ ከዚህ በከፋ እየተባባሱ መሆኑ ሀቅ ነው።

የጋራ ፌዴራላዊ ሀገር እንደ መሆኗ እና እንደ ባለድርሻ አካል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር/ኦነግ/ ችግሮቹ ከመባባሳቸው አስቀድሞ የተለያዩ የመፍትሔ ሀሳቦች እና መውጫ አማራጮችን ቢያቀርብም ሰሚ ጆሮ ያለው የሚመለከተው አካል ስላልነበር ዛሬ ሀገሪቱ ውጥንቅጥ ውስጥ ገብታ እያየን እንገኛለን።

ችግሮችን ለመቀልበስ እና ብሎም ውጤታማ ሰላማዊ ሽግግር እንዲኖር የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከትብብር ለህብረ ብሄር ፈደራሊዝም(ትህብፌ) ጋር በመሆን በሚያዝያ 2012 ሰፋ ያለ ሀሳቦችን የያዘ ሰነድ አቅርቦ ነበር።ሃሳቡም መንግስት በህገ መንግስቱ ማዕቀፍ ውስጥ የሆነ እና ወደ ሁሉን አቀፍ ሰላማዊ ሽግግር እንድያመራ የሚመክር ነበር።

የኛ ምክረ ሃሳብ በውስጥም በውጭም ችግር የገጠመው ሪፎርም እንዴት መመራት እንዳለበት፤የሚመለከታቸውን ባለ ድርሻ አካላት በማሳተፍ እና መግባባትን በመፍጠር ፖለቲካውን ማረጋጋት እና እንዴት በሂደት በህገ-መንግስቱ ማዕቀፍ ውስጥ የተረጋጋ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር መፈጠር እንዳለበት በግልጽ የሚጠቁም ነበር። ይሁን እንጂ ያቀረብነው የመፍትሔ ሀሳብ በገዥው ፓርቲ ተቀባይነት ሊያገኝ አልቻለም።

በድጋሚ በመስከረም 13-2020 ኦነግ በግልጽ በወጣ መግለጫ መንግስት በትብብሩ አባላት የተሰጡትን የመፍትሔ ምክረ ሀሳቦችን እንደገና እንዲያጤነው ፣ ብሎም ህግ እና ስርዓትን በተከተለ መልኩ የኢትዮጵያን ህዝቦች የቆየ ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ እንዲያደርግ እና ትብብሩም አብሮት ለመስራት ፈቃደኛ መሆኑን በመግለጽ ጠይቆት ነበር።ነገር ግን ገዠው ፓርቲ አሁንም ምክረ ሀሳቡን ውድቅ በማድረግ በተቃራኒው ዜጎችን በተለይ ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ደጋፊዎች እና አባላትን ማሳደድ፣ማሰር፣ማስጨነቅ እና በጭካኔ የተሞላ ዘግናኝ ግድያዎችን ማካሔዱን ቀጠለበት። በተለይ አፈናው እና ግድያው በኦሮሞ ነጻነት ግንባር/ኦነግ/አባላት ላይ እየተባባሰ በመሆኑ በዝያው መግለጫ አቤቱታችንን ለአፍሪካ ህብረት፣ለአውሮፓ ህብረት፣ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ም/ቤት እና ለተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በማስገባት ጉዳዩን በትኩረት አይተው ኢትዮጽያን ከህገ-መንግስታዊ ቀውስ እና ብጥብጥ ለመታደግ ጥብቅ እርምጃ እንዲወስዱ ጭምር ጠይቀናል።

በታህሳስ 12-2020 ኦነግ ባወጣው መግለጫ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት የተወሳሰቡ የፖለቲካ ሁኔታዎችን በመዘርዘር መፍትሄ ሊበጅላቸው እንደሚገባ አስጠንቅቆ ነበር። በመግለጫውም የክልሎች የመንግስት መዋቅሮች ፈርሰው ባሉበት፣ግጭት እና ጦርነት በተባባሰበት እና አለመረጋጋት በመላው ሀገሪቱ ላይ በሰፈነበት ሁኔታ ምርጫ ማካሄድ እንደማይቻል ገልጸን ነበር። በመሆኑም ከሚፈጠረው የፖለቲካ አለመረጋጋት እና የደህንነት ስጋት ራስን ለማዳን ብሎም ፖለቲካዊ ምክክር እና መግባባት

ለመፍጠር በኢፌድሪ ማዕቀፍ ውስጥ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የራሱን የኦሮሚያ ብሄራዊ የሽግግር መንግስት ለማቋቋም መዘጋጀት እንዳለበት ለህዝቡ አመላክተናል።

በሚያዝያ 07- 2021 ለአለም ማህበረሰብ ባሰራጨነው የዉስጥ ሜሞ የውጪ ሀይሎች እና የአማራ ሚሊሻ በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በመግባት ዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን እና ይህ ካልቆመ የሀገሪቱ ብሎም የአፍሪካ ቀንድ የደህንነት ጉዳይ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ አሳስበናል።

እንደ አለመታደል ሆኖ ገዥው ቡድን ያቀረብናቸውን ገንቢ ሀሳቦች ወደ ጎን በመተው አማራጭ የፓሌትካ ሀሳቦች ላይ በሮችን ዘጋ። በዚህም ሳይበቃ ንጹሃንን ማፈን፣ የጸጥታ ሀይሎችን በመጠቀም ተቃዋሚ ፖርቲዎችን ማሸበር እና ማሰሩን ተያያዘው። የሚፈጸምባቸውን የመብት ጥሰት በመቃወም የሚሰሙትን ድምጾች ለማፈን ህገወጥ ገደቦችን መጣል እና ወታደራዊ አገዛዝን እንደ መሳርያ መጠቀምን የዘወትር ተግባሩ አደረገ። በአሁኑ ጊዜ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ወሎን ጨምሮ አብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል በወታደራዊ አገዛዝ ስር ወድቀው ይገኛሉ።

እጅግ አሳዛኙ ደግሞ የሀገሪቱን 40% የሚሆነውን የኦሮሞ ብሔር የወከሉትን አነግ እና ኦፌኮን ከምርጫ ሂደቱ ተገፍተው እንዲወጡ ከማድረግ አልፎ በሀገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ላይ ተሳትፎ እንዳይኖራቸው ተደርጓል።

በማጠቃለያም በአሁኑ ጊዜ የሀገሪቱ የደህንነት ሀኔታ እና የፓለቲካ አለመረጋጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መሆኑ እጅግ አሳስቦናል። ሁኔታዎች መገመት በማይቻልበት ፈጥነት እየተባባሱ ለከፍተኛ ስርዓት አልበኝነት መንገስ በር ከፍቷል።

ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያሳተፈ ሀለንተናዊ የፖለቲካ ወይይት ካልተካሔደ፤መሪዎቻቸውን ጨምሮ የፖሌቲካ እስረኞች ካልተፈቱ፤አወዛጋቢውና ወዳቂ የሆነውን የምርጫ ህደት በድጋሚ እንዲታይ ካልተደረገ በሀገሪቱ የነገሰው ጽንፈኝነት እና ውጥረት በመባባስ ወደ ለየለት ስርዓት አልበኝነት እና ደም መቃባት ሊያመራ ይችላል ብለን እናምናለን።

ችግሮችን ለማቃለል የአለማቀፍ ማህበረሰብ እያከናወነ ስላለው ተግባራት እያመሰገንን ከጉዳዩ አሳሳቢነት የተነሳ አሁንም ተጨማሪ ስራ እንደሚጠበቅባችሁ እና ችግሮቹ ሁለንተናዊ መፍትሔ አስክያገኙ ጭምር የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ ጭምር ማስገንዘብ እንወዳለን።

በመሆኑም የአፍሪካ ህብረት/አሕ/፣ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ም/ቤት(የተመ) ፥ የአውሮፓ ህብረት /ኢዩ) እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ኦነግ ያቀረበውን ሀሳብ በአጽኖት በመቀበል ገዥው በድን ወታደራዊ ዘመቻውን በማቆም ወደ ባሰ ጥፋት አያመራ ካለው አካሄዱ ተመልሶ መፍትሔ ሊያመጣ ወደሚችለው ውይይት እንዲመለስ ጫና እንድታደርጉ ኦነግ ይጠይቃል።

ሀሌም እንደምንለው ውስብስብ ለሆነው የኢትዮጵያ ፓለቲካ ዘላቂና አስተማማኝ መፍትሄ የሚገኘው አካታች የሆነ የዲሞክራሲ ህደት መፈጠር እና ሀሉንም ተወካይ የፖለቲካ ሀይሎችን ያሳተፈ የፖለቲካ ምክክር ሲኖሮ ቢቻ እንደሆነ ኦነግ በጽኑ ያምናል።

በመጨረሻም አነግ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ለመስራት፤ ለፓለቲካ ውይይቶች ሁኔታዎችን ለማመቻቸት እና የፖለቲካ አቋም ልዩነቶችን በሰላማዊ አኮኋን መፍታት እና እና የጋራ መግባባቶችን በመፈጠር መጻኢ እጣ ፈንታ በመወሰን ላይ ጽኑ አቋም እንዳለው በአጽኖት መግለጽ እንወዳለን።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር/ኦነግ/

ሚያዝያ 28-2021

ፊንፊኔ/አዲስ አበባ

የኦነግ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ባቴ ኡርጌሳና ሹፌራቸው ወጣት ወንድወሰን አብዱልቃድር መታሰር አስመልክቶ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር መግለጫ
የኦነግ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ባቴ ኡርጌሳና ሹፌራቸው ወጣት ወንድወሰን አብዱልቃድር መታሰር አስመልክቶ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር መግለጫ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆነዉ አቶ ባቴ ኡርጌሳና ሹፌራቸው ወጣት ወንድወሰን አብዱልቃድር መጋቢት 20/ 2021 በኦሮምያ ልዩ ዞን ፊንፊኔ ዙሪያ ቡራዮ ፖሊስ ጣብያ ተይዘው መታሰራቸውን የኦነግ መገንዘብ ችሏል።

አቶ ባቴ ኡርጌሳ ያለምንም ጥፋት እና ወንጀል የታሰሩትን የኦነግ አመራርና ጓዶቹን በተደጋጋሚ ሂዶ ሲጠይቃቸው እንደነበረና በዚሁ እለት ጓዶቹን ለመጠየቅ በሄደበት በቡራዮ ፖሊስ ጣብያ መታስራቸውን ነው የተረዳነው። እንደማንኛውም የእስርኞቹ ቤተስብ እና ጓደኞቻቸዉን እንደሚጠይቁ ሁሉ አቶ ባቴም የሥራ ባልደረቦቹን ለመጠየቅ በሄዱበት ያለ አንዳች ጥፋት ከመስሪያ ቤት መኪና አሽከርካሪያቸው ወጣት ወንድወሰን አብዱልቃድር ጋር ፖሊስ ምንም አይነት የህግ አግባብ በሌለው ይዞ ያሰራቸው ሲሆን አቶ ባቴ እንደማንኛውም ዜጋ የታሰሩ ጓዶቹን የመጠየቅ መብት እንዳለው እናምናለን ።

ስለዚህ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አቶ ባቴ ኡርጌሳ፥ ሹፌራቸውና በተለያዩ ማጎሪያ ጣቢያዎች ታስረው ያሉ የኦነግ የፖለቲካ እስረኞች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ በአፅንኦት ይጠይቃል

በመጨረሻም መሰል ድርጊት በተለያዩ ቦታዎች በስፋት እየተደረገ ስለሆነ ከሃገሪቱ ህግ በሚጻረር ያለ አንዳች ጥፋትና ህጋዊ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ የኦሮሞያ ዜጎች እስር በአስቼኳይ እንዲቆም እናሳስባለን ።

ድል ለሰፊው ህዝብ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር

መጋቢት 21/2021

ፊንፊኔ

በአሁኑ ወቅት እየተከሄደ ያለውን ህገወጥ ጠቅላላ ጉባኤን በተመለከተ የኦነግ መግለጫ
መጋቢት 3 ቀን 2013 ዓ.ም                                                                                                                                                                         No:A6112/2011

ጥቂት አፈንጋጭ ቡድን በ ውጫዊ አካል አደረጅነት እና የፋይናንስ ድጋፍ በድርጅታችን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር/ኦነግ/ አመራር አባላት ስም በፈጠሩት ውዥንብር፣ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይህን ውዥንብር ለማጥራት እና በተለይም በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት መካከል ተፈጠረ የተባለውን አለመግባባት በተመለከተ ድርጅቱ ባለው ህገ ደንብ እና አሠራር መሠረት በጠቅላላ ጉባኤ እንዲ ፈታ መወሰኑ ይተወቃል። ለዚህም ቀደም ብለው በድርጅቱ ህገደንብ እና የውስጥ አሠራር መሠረት በብሔራዊ ምክር ቤት የተመረጡት የኦነግ ጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት ወደ ተግባር እንቅስቃሴ ገብቶ ይህንንም ለሚመለከታቸው አካላት በሙሉ፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ጨምሮ፣ በይፋ በኦፍሴላዊ ደብዳቤ አስተውቋል። በመሀከልም ኮሚቴው የደረሰበት ሁኔታ ለሚመለከታቸው አካላት እየስተወቃ፣ በተጨባጭ ያጋጠሙትን ፈታናዎችንም እንዲቀረፉለት ጥያቄ ሲያቀርቡ ነበር። የኦሮሞ ነፃነት ግንባርም ይህን የኮሚቴውን ጥያቄ ተንተርሶ በቀን 18/06/2013 ዓ.ም ለምርጫ ቦርዱ በፃፈው አቤቱታ ለጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ አስቻይ እና ምቹ የስራ ቦታ እንዲመቻች የድርጅታችን ዋና ፅ/ቤት እንዲከፈትልን መጠየቃችን የሚታወስ ነው።

በሐምሌ 25 ቀን 2012 ዓ.ም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያለ አንዳች የፍርድ ቤት ትእዛዝ በሃይል ዋና ፅ/ቤታችንን መዝጋቱ ይታወሳል። ከዚያ ቀን አንስቶ ዋና ፅ/ቤቱ በቅጥር ግቢው ውስጥ እና በዙሪያው የሚካሄደውን ማንኛውንም ተግባራት ለመቆጣጠር ያለ ህግ አግባብ ሀላፊነት በወሰደው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቁጥጥር ስር ይገኛል። ነገር ግን፣ በዛሬው ቀን በደረሰን መረጃ ላይ ተመሥርተን ድርጅታችን የማያውቀው ህገወጥ ስብሰባ በዋና ፅ/ቤታችን ሊደረግ መሆኑን አመልክተን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስቀድሞ ከቢሮ ሲያስወጣን በራሱ በወሰደው ሀላፊነት መሠረት በዓይኑ ፊት በአፈንጋጭ ቡድኖች እየተፈጸመ ያለውን ህገወጥ ተግባር እንዲያስቆም መጋቢት 3 ቀን 2013 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን በፃፍነው ደብዳቤ ጠይቀናል።

በድርጅታችን እምነት በአሁኑ ወቅት በዋናው ፅ/ቤታችን እየተካሄደ ያለው ስብሰባ ሙሉ በሙሉ ለአፈንጋጭ ቡዱኑ ሊፈቀድ የማይገባ ህገወጥ ስብሰባ ነው። ይህን ህገወጥነት እያወቀ ቆሞ የሚመለከት የህግ አስከባሪ አካልም ተጠያቂነቱ እየተወጣ እንዳልሆነ እንገነዘባለን። እነዚህ አፈንጋጭ ቡድን፣ በኦነግ ስም ጠቅላላ ገባኤ ለመጥረት ሆነ ለብቻቸው ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ ምንም ዓይነት ድርጅታዊ ውክልና እና ህጋዊ መሠረት የለቸውም። ይህ አካሄድ የድርጅታችን መተዳደሪያ ደንብንም ሆነ በአዋጅ 1162/11 የተደነገገውን የፖለቲካ ፓርቲ የጠቅላላ ገባኤ ስነስርዓት የተፃረረ ነው። በዚህ ላይ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንም በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ የውስጥ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ በመግባት ያለድርጅቱ ህጋዊ ተወካይ/ ያለሊቀመንበሩ/ እውቅናና ፍቃድ በተለይም ሊቀመንበሩን ጨምሮ ሁሉንም የድርጅቱ አመራሮችና የስራ ሀላፊዎችን ከህግ አግባብ ውጭ ከዋና ፅ/ቤት በኃይል በስወጣበት ሁኔታ፣ ጥቂት አፈንጋጭ ቡድንን አስጠልሎ ህገወጥ ስብሰባ በድርጅታችን ስም እንዲያካሂዱ ለመፍቃድ ምንም ዓይነት የህግ መሠረት የለውም።

ስለዚህም፣የኦሮሞ ነፃነት ግንባር/ኦነግ/ በድርጅታችን ላይ እየተፈፀመ ያለውን ነገር ህገወጥ፣ ኢፍትሐዊና ፖለቲካዊ ሸፍጥ መሆኑን ለመለው የኦሮሞ ህዝብ፣ ለኢትዮጵያ ህዝቦች እና ለዓለም ዓቀፍ ማህበረሰብ እያስታወቀ፣ የዚህ ዓይነቱ ግፍም ሀገሪቷን ወደ ከፋ ብጥብጥ ከመውሰድ ውጭ ለማንም መፍትሄ እንደማያመጣ አጥብቀን ለማስገንዘብ እንወዳለን። ለዚህም ህገወጥ ተግባር ዋና ተጠያቂው መንግስት እና ይህን ህገወጥ ተግባር በማስፈፀም ላይ ያሉት የመንግስት ተቋማት በመሆናቸው፣ ቁልፍ የመንግስት የፀጥታ፣ የፍትህ እና የዴሞክራሲ ተቋማት፣ብሔራዊ የምርጫ ቦርድን ጨምሮ፣ ነፃ እና ገለልተኛ ሆነው የሀገሪቱን ዜጎች አኩል እንዲያገለግሉ በአፅንዖት እያስገነዘብን፣ በተለይም የአዲስ የአበባ ፖሊስ ኮሚሸን ይህን ግዙፍ የህግ ጥሰት በአስቸኳይ እንዲያርም አበክረን እንጠየቃለን!

በመጨረሻም፣ የድርጅታችን አባላት እና ደጋፊዎች ከዚህ ህገወጥ የማጭበርበሪያ ስብሰባ ላይ ላለመከፈል ለሳያችሁት የሚያስደንቅ ትጋት እያመሰገንን፣ በቀጣይም ከደርጅታችሁ ጎን በመሆን በቁርጠኝነት ድርጅታችሁን እንዲትከላከሉና ዘብ እንድትቆሙለት ጥሪ እናቀርባለን!

ድል ለሰፊው ህዝብ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር

መጋቢት 3 ቀን 2013 ዓ.ም

ፊንፊኔ

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ የምርጫ ጉዳዮችን በተመለከተ በኦነግ የተሰጠ የፕሬስ መግለጫ
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ የምርጫ ጉዳዮችን በተመለከተ በኦነግ የተሰጠ የፕሬስ መግለጫ

(የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም)

ኦነግ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባደረገዉ ስምምነት ለአስርት አመታት የቆየውን ጠላትነት ነሐሴ 2010 ዓ.ም አቋርጦ የኦሮሞን ህዝብ የዲሞክራሲ

እና የራስን እድል በራስ የመወሰን ጥያቄ ቀጣይ ምዕራፍ በሰላማዊ መንገድ የፓለቲካ ትክል ለማከናወን መስከረም 2011 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ርዕሰ

መዲና አዲስ አበባ የኦነግ አመራር መመለሱ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ ህዝባችን አገሪቷ ከሚያዝያ 12/2018 እ.ኤ.አ ጀምሮ የገባችበትን የሁለት አመት

የሽግግር ሂደት መጠናቀቅን ተከትሎ በአገሪቷ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነፃ እና ፍትሐዊ ምርጫ ይካሄዳል የሚል እምነት ነበር፡፡

ነገር ግን እነዚህ ተስፋዎች ማቆልቆል ጀምረው ወደ ባዶ ደረጃ የወረዱት ብዙም ረዥም ጊዜ ሳይቆዩ ነበር፡፡ ተቃዋሚ “የፓለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገር

እንዲገባ መፍቀድ” የሚለውን ባነር ባነገበ ገዢ ቡድን ርካሽ የፓለቲካ ድል ግብ ከዋለ በኋላ ስርዓቱ ምንም ጊዜ አላባከነም፡፡ ኦነግ በመስከረም 5 ቀን

2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በጥቂት ቀናት ውስጥ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በማህበራዊ እና በመደበኛ ሚዲያ አማካይነት ይደረግበት

ጀመር፡፡

በእነዚህ የፕሮፖጋንዳ ጥቃት እና መረጃ ማሳሳት ዘመቻ ጫፍ ላይ እንዲሁም በኦነግ በኩል ውይይት እንዲደረግ ጥረቶቸ ቢደረጉም ስርዓቱ በምዕራብ

እና በደቡብ ኦሮሚያ ክፍሎች የወታደራዊ ዘመቻ ውስጥ ገብቷል፡፡ በነሐሴ 2010 ዓ.ም በተደረገው የአስመራ ስምምነት ላይ በተስማሙት መሰረት

ጦርነቱ እንዲያበቃ እና የኦነግ ሰራዊት የክልሉ ፖሊስ እና የደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ እንዲዋሃዱ የተደረሰውን ስምምነት ስርዓቱ ፈፅሞ ያልፈለገ

መሆኑን አሁን በግልፅ የታየ ጉዳይ ነው፡፡ የነፃነት ታጋዮቹ ከማህበረሰቡ ጋር በማዋሃድ እና ወታደራዊ የትጥቅ ትግሉን በተሳካ ሁኔታ ከማቆም ይልቅ

ስርዓቱ ኦነግ በሰላማዊ መንገድ ከሚያደርገው የፓለቲካ ትግል ከታጠቁት ሽምግ ተዋጊዎች ጋር የሌለውን ግንኙነት አለው ብሎ በሀሰት በመወንጀል

ከሰላማዊ ትግሉ ለመግፋት እንደመሳሪያ መጠቀምን መርጧል፡፡

የሚጠበቀው የነሀሴ ወር 2012 ዓ.ም ምርጫ ከመደረጉ በፊት ተቃዋሚዎችን በኦሮሚያ ውስጥ የማዳከም ስራው ቀጥሎ በተፋፋመበት ሁኔታ

የኮቪድ 19 በሽታ ተከስቷል፡፡ በሽታው በአገር አቀፍ ደረጃ ምርጫን ለማካሄድ አስቸጋሪ የሆኑ የተለያዩ ሁኔታዎችን ፈጥሮ እያለ ይህንን እንደመልካም

አጋጣሚ በመጠቀም ምርጫውን በተለያዩ የህግ እና የፓለቲካ ሂደቶች እንቅፋት ውስጥ ገብቷል፡፡ በህጋዊ መንገድ ሲታይ ህገመንግስቱ የፓርላማ

አባላት የስልጣን ዘመን ገደብ ለማራዘም ምንም አይነት ክፍተት ያልፈጠረ ቢሆንም የምርጫን ማስተላለፍ ጉዳይ ባሉት የፓለቲካ ሀይሎች አዲስ

የፓለቲካ ውሳኔ መወሰንን ያስፈልገዉ ነበር፡፡ ይሁንና ገዢው መንግስት እነዚህን ሀይሎች ያለምንም ጥርጥር በውሳኔው ላይ እንዳይሳተፉ አድርጓል፡፡

ይህንን ህገወጥ የስልጣን ማራዘም ተግባርን ለመቃወም እና ውድቅ የማድረግ ሂደት ከሁሉም አቅጣጫ በመፋፋሙ ምክንያት ገዢው ስርዓት በአሁኑ

ጊዜ በግራ ዘመም ፣ በቀኝ ዘመም እና በመሀል ሰፋሪ የተቃዋሚ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ተቃዋሚዎችን የመስበር ሂደቱን

የበለጠ ለማስቀጠል ብሩህ ልጃችን የሆነውን አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ እንደ መሳሪያ ተጠቅሟል፡፡ እስካሁን ድረስ የሀጫሉ እና የብዙ

የሌሎች ከፍተኛ የፓለቲካ ግድያ ድርጊቶች በገለልተኛ ሶስተኛ ወገን አልተመረመረም፡፡

በአገሪቱ የደቡብ አጋማሽ ላይ የክልል ራስ-ገዝነት እና የራስን እድል በራስ የመወሰን ፓለቲካን በሚያራምዱ ሁሉም ሀይሎች ላይ እንደዚህ አይነቱን

ከባድ የመበታተን እና የመሰባበር ተግባር በመፈፀም ገዢው ፓርቲ በፓለቲካ ድርድር እና ውይይት ከመፍታት ይልቅ የፓለቲካ ልዩነት በላቸው

ወገኖች ላይ በትግራይ ክልል የኦሮሚያ እና የሰፊው ደቡብ የአገሪቱ ክፍል ላይ የተፈፀመው የመበታተን ስራ ቀጣይ የሆነውን ጦርነት ከፍቷል፡፡ ኦነግ

የህውሀት ዝምድና እንደሌለዉ ህብረተሰቡ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ እኛ ከግብራበሮቻችን ጋር በመሆን ህውሃትን ከስልጣን ለማስወገድ እንዲሁም

አሁን አቋም በሌለው የኢህአዴግ መንግስት ላይ ትግል ስናካሂድ የነበርን ግንባር ቀደም የፓለቲካ ድርጅት ነን፡፡ ነገር ግን በመርህ ደረጃ አሁን

በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ኦሮሚያ ውስጥ ሲፈፀም ከነበረው ጭቆና ተስፋፍቶ የተዛመተ ጦርነት ነው ብለን እንገነዘባለን፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይን በተመለከተ በድርድር ለመፍታት ለአሜሪካ ገዢው ፓርቲ ስምምነት ደርሶ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስህተት

ከተፈፀመ በኋላ ኢትዮጵያ አጋሯን ሱዳን ያጣች ሲሆን እኛ አሁን ከሌላዋ የጎረቤት አገር ጋር ጦርነት ልንጋጠም አፋፍ ላይ እንገኛለን፡፡ ከፍተኛ

የፓለቲካ አመራሮችን ጨምሮ የዋና ዋና ተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች አባላት በገዢው ፓርቲ በዘፈቀደ ተይዘው የሚታሰሩበት፤ በፍርድ ቤቶች

ወይም በመንግስት አቃቤ ህግ መስሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ነፃ ተብሎ በሚለቀቁበት ጊዜ ጨምሮ በከፍተኛ አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ እንዲቆዩ

የሚደረግበት ሁኔታ የሚስተዋልበት አገር ውስጥ እየኖርን እንገኛለን፡፡ የተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች ጽ/ቤት – ከዋና መስሪያ ቤቶቻቸው ጨምሮ

በዘፈቀደ በገዢው ፓርቲ ተወሮ የሚያዝበት አገር ውስጥ እየኖርን እንገኛለን፡፡

እንግዲህ በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆና ነው አገሪቷ ለአቀር አቀፍ አጠቃላይ ምርጫ “እየተዘጋጀች” ትገኛለች፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው እያንዳንዱ አባላት ምርጫ ማለት የምርጫ ካርድ በኮሮጆ ውስጥ ስለምንከትበት ቀን የምናወሳበት ሂደት ብቻ አለመሆኑን

ለማስታወስ እንወዳለን፡፡ የምርጫ ጠቃሚው ጉዳይ ወደ ምርጫው ቀን የሚመራው ሂደት ነው፡፡ የዲሞክራሲ ስርዓትን ለመዘርጋት የመአዘን ድንጋይየሆነው የምርጫው ተአማኒነት በአብዛኛው የሁሉም የቅድመ ምርጫ ሂደቶች እና ተግባራት ላይ የሚወሰን ሲሆን ይህም ለተቃዋሚ የፓለቲካ

ፓርቲዎች ሀሳባቸውን የሚገልፁበት የተደላደለ ሜዳ መኖርን ያካትታል፡፡ ምርጫ በአጠቃላይ የምርጫ ካርድን በሚስጥር ወደ ኮሮጆ ወስጥ

ወደመክተቻ ቀን የሚያመሩትን ሂደቶች በአጠቃላይ የሚስተዋሉበት ሁኔታ ላይ ተመስርቶ የሚወሰን መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የምርጫ

ሂደት ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ገለልተኛ ነው ተብሎ እንዲወሰን የሚያደርግ ሂደት ላይ የሚመረኮዝ ነው፡፡ ይህ ሂደት በፓለቲካ ፓርቲዎች ሀሳባቸውን እና

ስራቸውን በነፃነት እንዲያሳውቁ፣ ለሁሉም ያለምንም አድሎ የሚያገለግል ገለልተኛ ሚዲያ መኖር፣ የምርጫ ቦርድ እና የፍትህ አካላት ገለልተኛ

ሆነው ማገልገልን የሚፈቅድ ቦታ የሚያዘጋጅ መሆን አለበት፡፡

ምርጫው ፍትሐዊ ገለልተኛ እና ተአማኒነት ያለው ለመሆነ ያነሰ እድል ያለው በመሆኑ ይህ ምርጫ ውጤቱ አስቀድሞ የታወቀ ምርጫ ነው፡፡

ለገለልተኛ ታዛቢ ከታየ ይህ ምርጫ እነዚህን መስፈርቶች አሟልቶ ያልቀረበ ፍፁም ምርጫ ሊባል የማይችል ተግባር ነው፡፡ ገዢው ቡድን ይህንን

ምርጫ ለማካሄድ የወሰነበት ብቸኛ ምክንያት በምርጫ ተመርጦ ስልጣን ላይ የወጣ መንግስት ለማስመሰል ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ በዛሬው ቀን

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቹ ለሚራብ ድሃ አገር ይህ አይነቱ በለጋሾች እና ባለሀብቶች ልገሳ የሚካሄደው ውድ ምርጫ ለማካሄድ ምንም ምክንያት

የለም፡፡

ከዚህ የተነሳ ኦነግ የሚከተለው እምነት አለው፡

1. በዲሞክራሲ ስርዓት ውስጥ የሚደረግ ነፃ እና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስፈልጉ ዝቅተኛ መስፈርቶችን ማሟላት ይቅርና የአገሪቷ

የአሁኑ ገዢ መንግስት በሌላው አገር የሚታዩ ነፃ ያልሆኑ የዲሞክራሲ ዝቅተኛ ደረጃዎችን እንኳን አያሟላም፡፡

2. ባለፉት 2 አመታት ከላይ በተጠቀሱት ሂደት ውስጥ በከፊል በመንቀሳቀስ የዚህ አይነቱ ምርጫ ውጤት ነፃ እና ፍትሐዊ ያልሆነ የሁሉም

ባለድርሻ አካላት ውክልና እና ተቀባይነት የሌለው ይሆናል፡፡

3. ምርጫው ከተካሄደም የአገሪቷን ዋና ዋና የፓለቲካ ችግሮች እና የግጭት ምንጮች የሆኑትን ችግሮች በመፍታት ረገድ ምንም አይነት ይህ

ነው የተባለ ልዩነት አያመጣም፡፡

ኦነግ ገዢው የብልፅግና ፓርቲ ሆን ብሎ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ለማሟላት ሆን ብሎ ያልፈለገ እንዲሁም ለራሱ እና ለአጋሮቹ በምርጫ

ውስጥ የማይገባቸውን ጥቅም ለማግኘት ሲባል ጆሮ ዳባ ልበስ ያለ በመሆኑ እና ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ለማሟላት ፈቃደኛ ባለመሆኑ

ምክንያት ለመሳተፍ ያልቻለ መሆኑን ሲገልፅ ሀዘን ይሰማዋል፡፡

ተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን ሰፊው ህዝብ የሚፈልገውን የሚከተሉትን ህጋዊ ጥያቄዎች ለማሟላቱ እና ለአገሪቱ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት

ግንባታ የሚያግዙ መስፈርቶችን ተግባራዊ ማድረግ ለሃገሪቱ ይጠቅማል ብለን እናምናልን፥

1. ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሁሉንም የፓለቲካ እስረኞችን መልቀቅ

2. በገዢው ፓርቲ እና እርሱ በሚቆጣጠረው የደህንነት ሀይሎች በአሁኑ ጊዜ የተዘጉ እና/ወይም በቁጥጥር ስር ያሉትን የተቃዋሚ ፓርቲዎች

ጽ/ቤት መልሶ መክፈት

3. በአገሪቱ ሁሉም ክፍሎች የሚስተዋሉትን ሁሉም ጦርነቶች በማቆም ሁሉን ያካተተ ድርድር እንዲደረግ

4. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የዳኝነት ስርዓት እና የህግ አስፈፃሚ አካልን ጨምሮ ቁልፍ የሆኑ ተቋማትን ገለልተኝነት እና ከአድሎ

የፀዱ መሆናቸውን ማረጋገጥ

5. ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የፖለቲካ ለዩነቶችን ለመፍታት ያለመ ወሳኝ የፓለቲካ ውይይት ሂደት ማስጀመር

ድል ለሰፊው ህዝብ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር

የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም

ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር የምርጫ ቦርድ የቦርዱ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ለሚድያ ተቋማት የስጠችውን መግለጫ በተመለከተ የተስጠ ወቅታዊ አቋም
ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር የምርጫ ቦርድ የቦርዱ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ለሚድያ ተቋማት የስጠችውን መግለጫ በተመለከተ የተስጠ ወቅታዊ አቋም

ጥር 2021 ዓም

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር እንደ ተፎካካሪ ሀገራዊ ፖለቲካ ፖርቲ ከምርጫ ቦርድ የምንጠብቀው ቢያንስ በገለልተኝነት ሀላፊነቱን እንደወጣ ነው። ይሁን እንጂ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ የምርጫ ቦርዱየኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ተወካይ በሚዲያ በቀረበች ቁጥር እውነት እና ሀቅን ለማዛበት የምትስጣቸው ኦነግን የተመለከቱ አስተያየቶች የገለልተኝነት መርህን የጣሱ መሆናቸውን እየተገነዘብን እንገኛለን።

በቅርቡ ከአሜሪካ ድምፅ አማሪኛ ፕሮግራም(በVOA ) ጋር በደረገችው ቃለምልልስ ሁለት በገሃድ የሚታዩ ትርክቶችን አዛብታ አቅርባለች፣ ለቦርዱም አመራር የሚደርሱት መረጃዎች እንዲህ የተዛቡ እና ቦርዱ ያለምንም ጭብጥ እና ከመረጃ ውጭ በዚህ ሁኔታ የሚገነዘቡ ከሆነ እጅግ በጣም ያሳስበናል። በዚሁ መስረት በድርጅቱ ውስጥ ያገጠሙትን የሃሳብ ልዩነት ተብየዉ በተመለከተ፣

1ኛ ” ሁለቱ ወገን ያስተላለፉት ህገወጥ እገዳ ነው ጣልቃ እንድንገባ ያስገደደን።”

2ኛ “የስነምግባር እና ቁጥጥር ኮሚቴያቸውም አለመግባባቱ ን መፍታት አለመቻሉን ገልፆልናል።” የማለት ቃል በቃልም ይሁን ይህን ይዘት ያለው አስተያየት ነው ለ VOA የተናገረችዉ። የተቋሙ የህዝብ ግንኙነት ትክክለኛውን እውነታ ባላማከለ መልኩ በዚህ ደረጃ የተሳሳተ መረጃ ማስገንዘብ የተቋሙን ክብር እና መልካም ሥነ ምግባር የሚያጎድፍ ሥራ ላይ የተስማራች በመሆኑ ከዚህ ድርጊት እንድትቆጠብ ከወድሁ እንመክራለን።

በተስጠው ቃለ ምልልስ መስረትም የመጀመሪያው ህገወጥ እገዳ የተባለው ቦርዱ በደብዳቤ ጠይቆን ያቀረብነውን ቃለ ጉባኤ ሳይመለከቱ እና በቃለ ጉባዔው የተካተቱትን ውሳኔዎች ያላዳስስ ሆኖ አግኝተናል ። ይህ ደግሞ ተገቢ አለመሆኑ ግልፅ ነው። በሽኝ ደብዳቤ ተደግፎ ለምርጫ ቦርዱ ፅ/ቤት ተልኳል ያለውን ደብዳቤ ለውሳኔ ሰጭ አካል ማቅረብ ያልቻለው አካል ኦነግን ህገወጥ እገዳ አድረክ ብሎ አስተያየት መስጠት ሀቅን ማዛባት ብቻ ሳይሆን ታማኝነት ማጉደል ጭምር መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን ።

ህገወጥ እገዳ በሁለቱም ወገን ተፈፅሞም ቢሆን ቦርዱ የቀረበለትን ውሳኔ ከድርጅቱ ህገ ደንብ አንፃር መርምሮ ውሳኔውን መቀበል ወይም ውድቅ አድርጎ በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት እንዲያደርጉት አቅጣጫ መስጠት እንጂ ጣልቃ የሚያስገባ ምንም ዓይነት ሕጋዊ መስረት አልነበረም። በሁለቱም ወገን የቀረበው ውሳኔን ማሳወቅ እንጂ አቤቱታም አልነበረም። በምርጫ ቦርድ አዋጅ መሠረት ደግሞ ቦርዱ ጣልቃ የሚገበው በሁለቱም ወገን አቤቱታ ሲቀርብለት ብቻ ነው። ከሁለቱ ወገን የቀረቡ ጣልቃ የመግባት ጥያቀዎች እስካልቀረቡ ድረስ ሕገ ወጥ እና አዋጅን የሚፃረሩ መሆናቸውን ማስንገዘብ እንፈልጋለን.

በእኛ እምነት በተከታታይም ለብዙ ግዜያት ለቦርዱ እደገለፅነው፣ ይህ ችግር በድርጅቱ የህግ ማዕቀፍ ውስጥ መፈታት ያለበት የውስጥ ጉዳይ ነው። በመተዳደሪያ ደንባችንም በግልፅ የተደነገገ የግጭት አፈታት ሥነሥርዓት፣ እርከኖች እና ስልጣን የተሰጠቸው አካል በግልፅ ተቀምጦ ያለ ለዘመናት ድርጅታችን ስንጠቀምበት የከረመ መሆኑ ግልፅ ነው።

በተጨማሪም የድርጅቱ ህገ ደንብ ተሟጦ ሳይተገበር ( “The principle of exhaustion ) በድርጅቱ ውስጥ ስልጣን ባለው አካል ሳይታይ ወደ ሦስተኛ ወገን እንዲደርስ ህገደንባችን አይፈቅድም የሚል ፅኑ አቋም አለን።

ስለዚህ ይህን ጉዳይ በተመለከተ በበኩላችን የቦርዱን ዳኝነት በማሸት ወይም ጣልቃ ገብነት በመጠየቅ ያስገባን አቤቱታ አልነበረም። እንደ ሕጋዊ አዋጁ የምርጫ ቦርዱ በሕግ እንደገለልተኛ ተቋም የሚጠበቅበትን እና የጠየቅነውን ብቻ ቢያደርግ ያስመሰግነዋል፤ መሆንም ያለበት እንደዛ ነበር። ይልቁንስ የአባሎቻችን በህገወጥ ሁኔታ በየቦታው መገደል መታሰር እና የቢሮዎቻችን ያለ ህግ መዘጋት በተመለከተ በሕግ የተስጣቸውን ቢያስፈጽሙ እስየው በተባለ ነበር ለምናቀርብ ጥያቀ እዛ ግባ የማይባል መልስ ሲስጡ ከርመዋል።

በተጨማሪም “የስነምግባር እና ቁጥጥር ኮሚቴ አለመግባባቱን በተመለከተ መፍታት አንችልም “ብለው ለቦርዱ ያስገቡት ሪፖርት አለ የተባለውንም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ምንም ከዚህ ጋር ተዛማችነት ያላቸውን ርፓርት በፍጹም አለቀረብንም መፍታት አንችልምም ተብሎ የተገለፀ የለም ። ይህን ለማረጋገጥ ደግሞ የድርጅቱ ስነምግባር ኮሚቴ በሕይወት እስካሉ ድረስ ማረጋገጥ ቦርዱን የሚሳነው ነው ብለን አናምንም። በዚህ ደረጀ የተሣሣተ መረጃ ለብዙሃን መገናኛ መስጠት ደግሞ የቦርዱን ስም እና የተቋቋመለትን ድርጅታዊ እንድምታ አይመጥንም። በአስቸኳይ መታረም እንዳለበትም በጥብቅ እንጠይቃለን። ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ የቦርዱ ሕዝብ ግንኙነት ሆነ ብለው ይኸን ሀቅ አዛብቷዋል። የድርጅቱ የስነምግባር ቁጥጥር ኮሚቴ ጉዳዩን መርምረው የደረሱበትን የውሳኔ ሀሳብ በጥቅሉ ለሚመለከታቸው ሕጋዊ አካል እና ለሕዝብ ጭምር ይፋ አድርጓል። ድርጅታችንም ለቦርዱም ይህን ሀቅ የውሳኔውን ጥቅል ሀሳብ ወደ አማርኛ አስተርጉመን በሸኚ ደብዳቤ አሳውቀናል። ቦርዱ የኮሚቴውን አባላት በፅ/ቤቱ ጠርቶ ባነጋገረበት ወቅትም ውሳኔ መስጠት አንችልም ብለው መልስ አልስጡም ፤ የሐምሌ 19 እና 20/2012 ስብሰባ ህገወጥ እንደነበረና ያን ተከትለው የተፈፀሙት ሂደቶች በሙሉ ህገወጥ መሆነቸውን በግልፅ ቋንቋ ነው የተናገሩት። ዝርዝር የውሳኔ ሀሳቡን ግን በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት ለሚመለከተው የድርጅቱ ውሳኔ ሰጭ አካል እንጂ ለቦርዱ ሪፖርት ማድረግ በድርጅቱ የውስጥ ድንጋጌ መስረት የማይፈቅድላቸው መሆኑን ነበር የተናገሩት። ይሆን እንጅ ይህን ውሳኔ ሐሳብ ከድርጅቱ ማጣራት ስቻል ይህን ሀቅ አጣሞ ማቅረብ ህዝባዊ ሀላፊነትን በሚገባ አለመወጣት ብቻ ሳይሆን ሆነ ብለው የግልን አድሎአዊ አቋም በተቋም ስም ለማራመድ መሆኑ ታውቆ ተጠያቅነት መኖር አለበት እያልን በመጨረሻም ድርጅታችን ኦነግ እነዝህ ተገዳሮቶች በዚህ ተጠያቂነት በጎደለው ሁኔታ የሚቀጥሉ ከሆነ ግን፣በበኩላችን እኛም በየጊዜው ለቦርዱ የሚንፅፈቸውን ደብዳቤዎች እና መርጃዎች ለህዝብ ግልፅ ለማድረግ እንገደዳለን።

ስለዚህ ምርጫ ቦርዱ በአዋጅ የተስጠውን የሕግ አግባብ ገለልተኝ በመሆን እንድወጣ እያሳስብን አሁንም ደግመን ችግሮቹን ለመፈታት የድርጅቱን የውስጥ ህግ ማቀፊን መከተል ተገቢ መሆኑን እንገልጻለን።

ድል ለስፊው ሕዝብ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር

ጥር 02/2021 ዓም

ለኦነግ ቀርቧል ስለተባለው ግልፅ ያልሆነ የስብሰባ ጥሪ መረጃው የለንም።
ለኦነግ ቀርቧል ስለተባለው ግልፅ ያልሆነ የስብሰባ ጥሪ መረጃው የለንም።

(የኦነግ መግለጫ -ጥቅምት 29,2020)

ነገ ጥቅምት 30,2020ዓም ለሚካሄደው ስብሰባ ለኦነግ ጥሪ ቀርቧል መባሉን በተመለከተ ድርጅታችን ኦነግ

የተደረገለት የስብሰባ ጥሪ ኣለመኖሩንና ኣንዳችም መረጃ ያልደርሰው መሆኑን ለአባሎቻችን እና ለመላው

ህዝባችን እንገልፃለን።

የተወሰኑ የኦሮሞ የሃገር ሽማግሌዎች በአካል ተገኝተው ነገ አርብ ሊካሄድ ነው ለሚባለው ስብሰባ ለኦነግ ጥሪ

መደረጉን አስመልክቶ እኛን በመጠየቃቸው ለመላው ህዝብ ተጨባጭ መረጃ ይደርስ ዘንድ ይህንን መግለጫ

ለማውጣት ተገደናል።

ኦነግን ጨምሮ ሌሎችንም የፖለቲካ ድርጅቶችና የሃገር ሽማግሌዎች እንደሚሳተፉበት በተገለጸው በዚህ

ስብሰባ ላይ እንዲካፈል ለኦነግ ጥሪ መደረጉን እና እንደሚሳተፍም እየተወራ መሆኑን ከነሱ ለመረዳት የቻልን

ሲሆን፡ ድርጅታችን ስለስብሰባው የሚያውቀው ነገር እንደሌለና እንዲሳተፍም የተደረገለት ጥሪ አለመኖሩን

ያስታውቃል።

የህዝባችን መብት እንዲከበር የማይፈልጉ የትግላችን እንቅፋት የሆኑ አካላት እና ቡድኖች ህዝባዊው

ተቃውሞና ትግል ሲያስጨንቃቸው ሊቃውንትና ሸማግሌዎችን እንደመሳሪያ ተጠቅመው በማወናበድ

በህዝብ ላይ የባርነት እድሜያቸውን ማስረዘምን ሁሌም እንደስልት መጠቀም ባህላቸው ነው።

የኦሮሚያ ዜጎች እያጋጠማቸው ላለው አለመረጋጋት እና ከባድ የደህንነት ስጋት ዘላቂ መፍትሄ ለማስገኘት

እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ጊዜ ኦነግ ያልሰማውን ጉዳይ እንደተነገረው አድርገው ለማቅረብ መሞከር የህዝብ

ድጋፍ ማጣታቸውን በግልፅ ያሳያል። በተጨማሪም ለውስብስቡ ችግሮች የመፍትሄ ሃሳብ በማቅረብ የትግል

ኣመራር በመስጠት ላይ የሚገኙትን እንደኦነግ ያሉ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶችን እንዲሁም የተከበሩ

ሊቃውንቶች እና ሸማግሌዎችን በሚባለው መድረክ ላይ በማቅረብ በተሳሳተ ፕሮፓጋንዳ ሊነጉዱባቸው ነው

ብለን እናምናለን።

ይህ አይነት አካሄድ የአገሪቱን ዜጎች አንቆ ለያዘውና የህዝብን ደህንነት በበለጠ ወደከፋ አሳሳቢ ሁኔታ

እየወሰደ ላለው ችግር መፍትሄ ይሆን ዘንድ ለቀረበውና በህዝብም ከፍተኛ ምተቀባይነት ያገኘውን በሳል

የመፍትሄ ሃሳብ መልስ በመስጠት የሽግግር መንግስት ምስረትን ከመደገፍ ይልቅ፡ በተለያየ ድራማ

ውዥንብር በመፍጠር እውነታን አድበስብሰው በህዝብ ጫንቃ ላይ ለመቆየት መገላታቱ ትልቅ ኪሳራ ነው።

በድጋሚ በአባ ገዳዎች እና በሽማግሌዎች ይገኙበታል በሚባለውና ኦነግም እንደተጋበዘ ስለሚነገረው ግልጽ

ያልሆነ ስብሰባ ምንም መረጃ እንደሌለን ለሁሉም እየገለፅን ላለው ችግር ዘላቂ መፍትሄ የሚሆነው ኦነግ

ላቀረበው የኦሮሚያ ብሄራዊ ሽግግር መንግስት ጥሪ በጎ ምላሽ በመስጠት ሽግግሩን እውን ማድረግ እንደሆነ

እናሳስባለን።

ድል ለሰፊው ህዝብ!

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር

ጥቅምት 29, 2020ዓም

በኦሮሚያ በወጣቶች ላይ ተነጣጥሮ እየተፈጸመ ያለው ግድያ የደህንነት ስጋት እየተባባሰ በመሄድ ላይ መሆኑን ያመልክታል
በኦሮሚያ በወጣቶች ላይ ተነጣጥሮ እየተፈጸመ ያለው ግድያ የደህንነት ስጋት እየተባባሰ በመሄድ ላይ መሆኑን ያመልክታል

(የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መግለጫ –ጥቅምት 25, 2020ዓም)

በመላው ኦሮሚያና በኣፍሪካ ቀንድ ቀጣና ላይ ባጠላው የደህንነት ቀውስ ህዝቡ በከፍተኛ ስጋት በተዋጠበትና እንደኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) ያሉ ለህዝባቸው መብት የሚፋለሙ የፖለቲካ ድርጅቶች ለመፍትሄው ጥረት በማድረግ ላይ ባሉበት በዚህ ወቅት በወጣቶች ላይ ተነጣጥሮ እየተካሄደ ያለው ዘመቻ ችግሩ እየተባባሰ በመሄድ ላይ መሆኑን ያመላክታል።

ኦነግ የዛሬው የነጻነት ትግል ዋስትናና የነገው ኦሮሚያ ተስፋ በሆኑ የኦሮሞ ወጣቶች ላይ ያተኮረው ግድያ በማናቸውም ኣካል ይፈጸም የሃገሪቷን ህጎችና ህገ-መንግስቱን፣ የኣለምኣቀፍ ስምምነቶችንና ሰብዓዊ ክብርን የጣሰና ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ በጥብቅ ያወግዛል።

ሰሞኑን በደቡብ-ምስራቅ ኦሮሚያ ባሌ-ሮቤ፣ በምስራቅ ኦሮሚያ ኣወዳይና መቻራ እንዲሁም በምዕራብ ኦሮሚያ ነቀምቴ ከተማና በመላው ኦሮሚያ በኦሮሞ ወጣቶች ላይ በጠራራ ጸሃይ እየተፈጸመ ያለው ዘግናኝ ግድያ የኦሮሚያ ሰላምና ደህንነት ያለበትን ኣስከፊ ደረጃ በግልጽ ያሳያል።

የመንግስት መዋቅር በነበሩ የተለያዩ ኣካላት እንደተፈጸመ የህዝቡ እምነት የሆነው- የኦሮሚያ ወጣቶችን ከጎዳና ላይ፣ ከመኖሪያ ቤታቸው ኣውጥቶና ከተለያዩ ቦታዎች ኣድኖ የመግደል ዘመቻ፥ ህዝቡ የደህንነት ዋስትና እንደሌለው የሚያመላክት ከመሆኑም ማሻገር የኦሮሞን ትግል ለማደናቀፍ ሲሰሩ በነበሩ ኣካላት ተቀነባብሮ በመካሄድ ላይ ያለ ዘመቻ ነው ብለን እናምናለን።

ስለሆነም ህዝባችንና ባጠቃላይ የኦሮሚያ ዜጎች ወጣቶችን ከምድረ-ገጽ ለማጥፋት ያለመውን ይህንን እኩይ ሴራ በጋራ በንቃት እንዲጠብቁ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

መላው የደህንነት ሃይሎች ኣባላት የሆናችሁ ሁሉ ከዚሁ ህዝብ ኣብራክ ነው የወጣችሁት፣ ቤተሰቦቻችሁና ዘመዶቻችሁም የሚኖሩት ከዚሁ ህዝብ ጋር ነው። በመሆኑም ታማኝነታችሁ ከኣብራኩ ለወጣችሁት፣ ኣብራችሁት ለምትኖሩትና ደህንነቱን ለማስጠበቅም ቃል ለገባችሁት ህዝባችሁ መሆኑን ተገንዝባችሁ፥ መሰል ወንጀሎችን ከመፈጸም እንድትቆጠቡና ህዝቡንም ከወንጀለኞች እንድትጠብቁ ወገናዊ ጥሪያችንን ኣጥብቀን እናቀርብላችኋለን።

ለኦሮሚያ ዜጎች መብት የምትታገሉ የፖለቲካ ድርጅቶችና ታጋዮች፣ መንግስታዊ ያልሆኑና የግል ተቋማት፣ የሙያና የሲቪክ ማህበራት ባጠቃላይ ኦሮሚያ ዜጎች፥ ህዝባችንንና ሃገራችንን ከተነጣጠረበት ከባድ ኣደጋ ለመታደግ የኦሮሚያ ብሄራዊ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ኦነግ ላቀረበው ጥሪ በጎ ምላሽ ሰጥታችሁ በማሳካት ግዴታችሁን እንድትወጡ በድጋሚ እናሳስባለን።

በመጨረሻም እየተፈረካከሰ ባለው የመንግስት መዋቅር ቡድን የተለያዩ ኣካላት በየቦታው በህዝብ ልጆች ላይ ተነጣጥሮ በመፈጸም ላይ የሚገኘው የግድያ ዘመቻ ህዝቡ ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲ፣ ለሰብዓዊ መብት መከበርና ለነጻነቱ መረጋገጥ እያካሄደ ያለውን ትግል ኣንዳች እርምጃ ወደኋላ የማይመልስ መሆኑን እያሳሰብን፡ ይህን ወንጀል የሚፈጽሙትና የሚያስፈጽሙትም ከታሪክና ከህግ ተጠያቂነት የማያመልጡ መሆኑን ኦነግ ለሁሉም ለመግለጽ ይወዳል።

ህዝባችን ከመታደን፣ ከመታሰር፣ ለሰቆቃ ከመዳረግና በኣሰቃቁ ሁኔታ መገደልን ጨምሮ በብዙ መልክ ከሚካሄድበት ዘመቻ ነጻ ሊወጣ የሚችለው የኦሮሚያ ብሄራዊ የሽግግር መንግስትን ኣቋቁሞ የኔ ነው ብሎ እምነት የሚጥልበት መንግስት ሲመሰርት ብቻ መሆኑን እያሳሰብን። ለዚህም ትግሉን እያጠናከረ ከተለያየ ኣቅጣጫ ለተደቀነበት የጠላት ጥቃት ለራሱ ጠንካራ ጥበቃ እንዲያደርግ በዚሁ ኣጋጣሚ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

በወጣቶች ላይ በማነጣጠር በመላው ኦሮሚያ ውስጥ ለሁለት ዓመታት ሲካሄድ የቆየው፡ በመካሄድም ላይ የሚገኘው ግድያ የደህንነት ስጋቱን ይበልጥ ወደ ከፋ ደረጃ እያሸጋገረው መሆኑን ህዝባችን ተረድቶ ለመፍትሄው እንዲንቀሳቀስ እናሳስባለን።

ድል ለሰፊው ህዝብ!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር

ጥቅምት 25, 2020ዓም

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግሮችና መሰረታዊ መፍትሄው
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግሮችና መሰረታዊ መፍትሄው

(Civil Political Discourse for Ethiopian Peoples)

ኢትዮጵያ በኣሁኑ ወቅት የገባችበት የፖለቲካ ችግር በተለይም ደግሞ በኦሮሚያ እየታዩ ያሉት ውስብስብ ችግሮች ኦሮሚያን የቀውስና ጦርነት ኣውድማ በማድረግ ኣለመረጋጋት እንዲኖር ማድረግ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ከማትወጣበት ጥፋት እየዘፈቃት ነው። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ ኣስተዳደር ስር ይገኛል። የፖለቲካ ችግር በወቅቱ ባለመፈታቱ የተነሳ የቀድሞው የመንግስት መዋቅር ተበጣጥሷል። በኣሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ውስጥ የህዝቡን ችግር የሚፈታ የተመረጠ የአስተዳደር ኣካል የለም። ህዝቡ ሲገደል፣ ሲዘረፍ፣ ንብረቱ ሲወድምበት ስሞታውን ኣቅርቦ መፍትሄ የሚያገኝበት ቦታ ኣጥቷል። ይህ እንዲሁ ከቀጠለ ከዚህ የባሰ ኣስከፊ ችግር ሊከተል ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ ኣካላት መንቀሳቀስ ለኦሮሚያ መፈራረስና ልንወጣው ከማንችለውና ኋላም እንዴት መያዝ እንደሚቻል ወደማናውቀው ችግር ይከተናል።

የኦሮሚያ መፈራረስ የኦሮሞን ህዝብ ብቻ ሳይሆን በኦሮሚያ ዜጎች ላይ የማያቋርጥ ችግር ማስከተሉ ይታወቃል። ከግለሰብ ኣንስቶ እስከቤተሰብና ሃገር ድረስ በኢትዮጵያ ከባድ እየመጣ መሆኑን ማንም ሊክደው ኣይችልም። ስለሆነም ኣስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት ለማስገኘት ኣስቸኳይ መፍትሄ ማፈላለጉ በእጅጉ ኣስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

ኦሮሞና የኦሮሚያ ዜጎች በርካታ ጉዳዮችን ይጋራሉ። ኣንድ ሃገር፣ ኣንድ የኑሮ ሁኔታ፣ ተመሳሳይ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ችግሮችና ባህልን መጋራታቸው ለረጅም ዓመታት የነበረ ነው። በተለይም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል ያመጣብንን ሁሉንም ችግር ከትውልድ ትውልድ ተሸጋግሮ ኣብረን ስንታገላቸው እንደነበርንና ኣሁንም በመታገል ላይ እንዳለን ይታወቃል። ይህም ኦሮሞ ከሌሎች ዜጎች ጋር ያለው ግንኙነት ይበልጥ ጠንካራ መሆኑን እያሳየ ነው።

ካሁን ቀደም በበርካታ ትግል ውስጥ ኣብረን ኣሳልፈን እዚህ እንደደረስነው፡ ኣሁንም ኦሮሞና የኦሮሚያ ዜጎች እጅ ለእጅ ተያይዘን ኣብረን በመስራት የጋራ የሽግግር መንግስት በመመስረት ከዚህ ችግር ለመውጣትና በጋራና በየግል ያለንን ዓላማ የምናሳካበት ጊዜ ኣሁን ነው ብለን እናምናለን። ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ብሄሮችና ብሄረሰቦች የኦሮሚያ ክልልን በማረጋጋቱ ረገድ የበኩላችሁን ድርሻ በመወጣት በኦሮሚያ ውስጥ የሚኖረውን ዜጋችሁን መታደግ ብቻ ሳይሆን እንደሃገር በጋራ ያለንን መሰረት ለማድረግ ይረዳላን የሚል እምነት ኣለን።

የኦሮሚያ መፈራረስ የሚያስከትለው ችግር በእጅጉ ሰፊ ነው። ችግሩ የኦሮሞና የኦሮሚያ ዜጎች ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያና የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ችግር እንደሆነ መገንዘብ ኣለብን።

ስለሆነም ኣሁን ባለው ሁኔታ ውስጥ የኦሮሚያ ብሄራዊ የሽግግር መንግስት በኣስቸኳይ መመስረት ወሳኝ ሆኖ ተገኝቷል። መረዳት ያለብን ቢኖር የሽግግር መንግስት መመስረቱ ሃገርን ለማፈርረስ ሳይሆን ከመፈራረስ ለመታደግ፣ ከተጋረጠው ኣደጋ ሃገሪቷንና የኣፍሪካ ቀንድ ቀጣናን ለማዳን መሆኑን ለኢትዮጵያ ህዝቦች፣ ለኣፍሪካ ቀንድ ሃገራትና ለኣፍሪካ ኣህጉር እንዲሁም ለኣለም መንግስታት ማረጋገጥ እንሻለን።

በታሪክ ኦሮሞ ሃገር ኣፍርሶ ኣያውቅም፡ ይገነባል እንጂ፣ ኦሮሞ ለራሱ ብቻ ኣስቦም ኣያውቅም ብሄር ብሄረሰቦችን ኣሰባስቦ ኣብሮ መኖር እንጂ። ለዚህም ዋነኛው ምስክር ከኢትዮጵያ ውስጥ ከሁሉም በላይ ብሄሮችና ብሄረሰቦችን በብዛት ያቀፈው ኦሮሚያ መሆኑ ነው። ስለዚህ ኦሮሚያ በርካታ ብሄሮችና ብሄረሰቦች የሚገኙባት ኢትዮጵያ ተምሳሌት ነው ለማለት እንችላለን። የሽግግር መንግስት ማቋቋሙ በኦሮሚያ ውስጥ ለሚኖሩ ብሄሮችና ብሄረሰቦችን ደህንነት ለመጠበቅ፣ ኣንድነታቸውንና ኣብሮ መኖራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ኣስፈላጊ ነው። በመሆኑም ይህ የሽግግር መንግስት በታሪክና በባህል የተገነባውን ይበልጥ ለማጠናከር እንጂ ጥፋትና መፈራረስን ለመፍጠር እንዳልሆነ በድጋሚ ማረጋገጥ እንሻለን። በኦሮሞና በሌሎች የኦሮሚያ ዜጎች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር፣ ፍቅርን ለማጎልበትና ኣብረን ሃገር በመመስረት ላይ በመመርኮዝ ኣብረን መጓዝ እንሻለን። ይህ ለሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎችም የኣስተማማኝ ሰላም መሰረት ይሆናል ብለን እናምናለን።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦሮሞና ሌሎችም የኦሮሚያ ዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮኣችሁን እየጎዳ ያለውን ውስብስብ ችግር ኣብረን ልንፈታ እንችል ዘንድ ጥሪውን ያቀርብላችኋል። ለመላው ኦሮሞና የኦሮሚያ ዜጎች እያቀረብን ያለው ይህ ጥሪ በኣሁኑ ወቅት የሚመሰረተው የሽግግር መንግስትም በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከህዝቡ፣ በህዝቡ ህዝብን ለማገልገል የተመረጠ መንግስት(government of the people by the people for the people) ለማቋቋም ወሳኝ መሰረት የምንጥልበትና ሁኔታ የምናመቻችበት ጊዜ ነው። መጻዒያችን ትንሽ ትልቅ ብሎ ሳይለይ ሁሉም የኦሮሚያ ዜጎች ድምጻቸው ዋጋ የሚገኝበት እንደሚሆን እርግጥ ነው።

ዓላማችንና የሽግግር መንግስቱ ግብ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረውን ኣድልዖኣዊ የፖለቲካ ባህል(partisan political culture) ቀይረን በህዝቡ ተመርጦ ህዝቡን በሚያገለግል ሁሉንም የኦሮሚያ ዜጎች ያቀፈ መንግስት ለመተካት መሆኑን ማረጋገጥ እንሻለን።

ኦነግ የፖለቲካ ዓላማውን ሰው ላይ የሚጭን ሳይሆን የተለያዩ ኣካላትን ኣድምጦ ለሁሉም ዜጎች በሚሆን መልኩ የጋራ የኣስተዳደር ኣካል በመመስረቱ ላይ ጥረት ያደርጋል። ይህንንም እውን ለማድረግ መሰረቱን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ ከሁሉም የኦሮሚያ ዜጎች ጋር ኣብረን እንድናበጅ ማሳሰብ እንወዳለን። ይህም ለሁላችንም ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ያስገኛል ብለን እናምናለን።

የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል ቀይረን በኦሮሚያ ላይ ኣስተማማኝ መረጋጋት ያለበት፣ ሁሉን ያቀፈ፣ ሁሉንም የሚያከብርና እኩል የሚያገለግል መንግስት ከመሰረትን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሃገራችን ምን እንደምትመስል ሁላችንም መገመት እንችላለን።

በዜጎች እኩልነትና በህዝብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ መንግስት ከተቋቋመ፣ ግልጽ የሆነ የብሄራዊና የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ ካለ፣ ህግ ኣውጪና ህግ ኣስፈጻሚው ኣካል ተለይቶ ከተቋቋመ፣ ሰላምን የሚያስጠብቅና ሃገርን የሚከላከል ኣካል ስልጣን ላይ ባሉ ኣካላት የማይነዳ ከሆነ፣ መንግስት ለፈጸመው ጥፋት ሃላፊነት ካለው፣ ሰብዓቂ መብት እንደግለሰብና በጋራ ከተከበረ ሃገር ዜጎቿ በሰላምና በደስታ የሚኖሩባት ትሆናለች ብለን እናምናለን።

ሰላምና መረጋጋት ካለ ብሄሮችና ብሄረሰቦች ይህ ሃገር የኔ ነው፣ ይህ የኔ መንግስት ነው ብለው ካመኑ እድገትና ብልጽግና ማምጣት ኣያስቸግርም። ሃገራችን ለምና የኣለም ኢንቨስትመንትን የምትስብ ናት። ይሁን እንጂ ሰላምና መረጋጋት ከሌለ ኢንቨስተሮች ይሸሹናል። የሃገር ውስጥም ይሁን የውጪ ባለሃብቶች ያለኣንዳች ስጋት እንዳሻቸው ኢንቨስት ማድረግና ሃገራችንን ከልመና ልናላቅቅ የምንችለው ሰላምና ኣስተማማኝ መሰረት ያለው መንግስት ሲኖር ብቻ ነው። ሰላምና የተረጋጋ ህዝባዊ መሰረት ያለው መንግስት ሲኖር ብቻ ነው ወጣቶችና የተማረው ሃይል በስራ ሃገርን ወደ መለወጡ ሊሰማራ የሚችለው። ይህ ሲሆን ነው ሰው በሰላም ወጥቶ ሰርቶ ቤተሰቡን ማኖት የሚችለው፥ የግልና የጋራ ሃብት ዋስትና የሚያገኘው፣ ልጆቻችን በሰላም ወጥተው ተምረውና ሰርተው በሰላም ይገባሉ፣ ከጥላቻና ጦርነት ይልቅ ፍቅርና መተጋገዝ በህዝባችን መሃል ይሰፍናል። የመረዳዳትና መደጋገፍ ባህላችንንም መልሰን ልንገነባ እንችላለን።

በመጨረሻም በኣሁኑ ወቅት ሃገራችንን ያጋጠማት የፖለቲካ ችግር በእጅጉ ውስብስብ ነው። በበሰበሰውና ለበርካታ ዓመታት በዘለቀው የፖለቲካ ባህል ስር ይህን ውስብስብ የፖለቲካ ችግር መፍታት ኣልተቻለም። ኣያሌ ጊዜያት ተሞክሮ፣ በርካታ ህይወት ተከፍሎበት፣ በርካታ ሃብት ወድሞበት ኣልተሳካም። ይህንን ውስብስብ ችግር ተገናኝተን በመወያየት የመፍትሄ መንገድ ካበጀን ብቻ ነው ልንወጣው የምንችለው። ኣሁን ያለው ኣንዱና ብቸኛው የመፍትሄ መንገድ ለሌሎች መንግስታትና ክልሎችም የሰላም መሰረት የሚሆን ብሄራዊ የኦሮሚያ የሽግግር መንግስት የኦሮሚያ ዜጎች በጋራ ማቋቋሙ ነው። ይህም የበኩላችንን ተሳትፎ የምናደርግበትና ፍላጎታችንን የምንገልጽበት ይሆናል። እንዲሁም ኣሁን ያለንበትን የሰላምና መረጋጋት ችግር መፍታት የምንችለው ተገናኝተን በመወያየት ብሄራዊ የኦሮሚያ የሽግግር መንግስት ካቋቋምን ብቻ ይሆናል።

ኦነግ የሽግግር መንግስቱን ምስረታ ስራ ላይ ለማዋል ባለው ኣቅም ሁሉ ለስካታማነቱ በመስራት ላይ መሆኑን ያረጋግጣል። የህዝቡንና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ኣካላትን ሃሳብ ወስደን ለህዝቡ በሚሆን መልኩ በጋራ ኣስተዳደር ለማቋቋም ሁሌም ዝግጁ መሆናችንን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የኦሮሚያ ብሄራዊ ሽግግር መንግስት ምስረታ ሂደትን በተመልከተ በተለያየ መንገድ ከናንተ ጋር ግንኙነት በመፈጠር ስራ ላይ በማዋሉ ኣብሮኣችሁ ተወያይቶ እንደሚሰራ ያረጋግጥላችኋል።

በመጨረሻም ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ለዲሞክራሲ መብት፣ የህዝቦች መብት እንዲከበርና ለብሄሮችና ብሄረሰቦች እኩልነት መረጋገጥ በመፋለሙ ላይ ህይወታቸውን ለሰዉ የኦሮሚያ ዜጎችና ለሌሎችም ብሄር ብሄረሰብ ዜጎች ሁሉ ያለኝን የላቀ ክብር መግለጽ እወዳለሁ። በተለይም ዘልዓለማዊ ክብር ለዚህ ላበቁን ታጋዮቻችን ይሁን።

እንዲሁም ሃገርን ለመታደግ፣ ከህዝቡ ጎን የቆሙና ሰላምን ለማውረድ ሲፋለሙ ህይወታቸውን ላጡ የደህንነት ሃይሎች ታላቅ ኣክብሮት ለመስጠት እወዳለሁ። በተለይ የሰብዓዊ ክብር ጠብቃችሁና ስራችሁን በህጉ ኣግባብ በማከናወን ኣሁን ባለው ኣስቸጋሪ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ቤተሰቦቻቸውንና ኑሮኣቸውን ትተው ሌትተቀን የህዝቡን ደህንነት በመጠበቅ ላይ ያሉትን የፊንፊኔ(ኣዲስ ኣበባ) ፖሊስና ደህንነት ሃይሎችን በእጅጉ አደንቃለሁ፥ ኣከብራለሁ።

እንዲሁ እንደግለሰብ፣ እንደቡድንና እንደተቋም ከጎናችን በመቆም ጽናታችንን ይበልጥ ኣጠንክረን ኣሁን ያለንበት ቦታ

እንደንደርስ ላደረጋችሁን ሁሉ ምስጋናዬን ኣቀርባለሁ።

ለኦሮሚያ ብሄራዊ የሽግግር መንግስት መቋቋም ጥሪ ካቀረብን ወዲህ ጥሪውን ተቀብላችሁ ከጎናችን በመቆም ለስኬታማነቱ ከኛ ጋር የተሰለፋችሁትን ከዚህ በታች ያላችሁንም ላመሰግን እወዳለሁ፡

1. ይህንን ጥሪያችንን ተቀብላችሁ ከኛ ጋር የቆማችሁ የተከበራችሁ የኦሮሚያ ዜጎች

2. የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለይም ኣጋራችን የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ(ኦፌኮ)

3. በሃገር ቤትና በውጪ ሃገራት ለሚገኑ የኦነግ ኣማራር

4. በሃገር ቤትና በውጪ ሃገራት ለሚገኙ የኦነግ ኦፊሰሮች

5. ለቄሮ ቢሊሱማ ኦሮሞ

6. ለደጋፊዎቻችንና ለኦሮሞ ማህበረሰብ

7. ለኦሮሞ ምሁራን ቡድን(The Oromo Scholars and Professional Group)

8. ለኦሮሞ ግሎባል ፎረም(Oromo Global Forum)

9. ለህዝባችን ድምጽ ለመሆን ጥሪ ላቀረባችሁ የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች

10. ለግሎባል ኦሮሚያ የጋዜጠኞች ማህበር(Global Oromiyaa Journalist Association)

11. ለአለም-ኣቀፍ የ39 ንቅናቄ ድጋፍ ቡድን

12. የኦሮሚያ ዜጎች የፖለቲካ እስረኞችን ለማስፈታት ተደራጅታችሁ እንቅስቃሴ ለጀመራችሁ የኦነግ ኣባላትና ደጋፊዎች ኮሚቴ

13. እንዲሁም ስማችሁ ያልተጠቀሰ ሁሉ

ስላዳመጣችሁኝ ኣመሰግናለሁ።

ድል ለሰፊው ህዝብ!

ዳዉድ ኢብሳ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ-መንበር

ጥቅምት 8, 2020ዓም

ፊንፊኔ(አዲስ ኣበባ), ኢትዮጵያ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መግለጫ
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መግለጫ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በሃገሪቷ በተለይም በኦሮሚያና በኣማራ ክልል ውስጥ ባሉ ችግሮች ላይ ከሌሎች የኦሮሞና የኣማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ማካሄዱ ይታወሳል።  ውይይቱም በፓርቲዎቹ ኣበይት የፖለቲካ ኣጀንዳዎች፣ በዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተለይም በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ በተፈጸሙ ግድያና እስራት እንዲሁም በኦሮሚያና በኣማራ ክልል በመንሰራፋት ዜጎችን ለከፋ ሰቆቃ በመዳረግ ላይ ያሉ ችግሮችን መፍታት በሚቻልበት ላይ ያተኮረ ነበር።

ይሁንና ከሁለት ወራት ወዲህ ከኣርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ በተከሰቱ ውስብሰብ ሁኔታዎችና ከተፈጠሩ ችግሮች የተነሳ ውይይቱ እንደታሰበው ሊሄድ ባለመቻሉ ኦነግ ከውይይቱ መካፈሉን ሊገታ ቻለ።

የኦሮሞና የኣማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኦሮ-ኣማራ ስም መስከረም 23, 2020ዓም ተሰባስበው ስምምነት ተፈራረሙ በሚል በወጣው መግለጫ ላይ ኦነግ እንደተሳተፈ ተደርጎ ስማችን መነሳቱ ተገነዘብን። ይህ ሊታረም የሚገባው ስህተት ነው።

የውይይቱ መጀመር ያለ ቢሆንም፡ ትላንት በተካሄደውና ኦነግ ባልተካፈለበት መድረክ ላይ መቋጫ ላይ የተደረሰ ስምምነት በሚል ኦነግ በመድረኩ ላይ እንደነበረ በማስመሰል የወጣው መግለጫ ድርጅታችንን የማይወክል መሆኑን ለሁሉም እንገልጻለን።

ድል ለሰፊው ህዝብ!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር

መስከረም 24, 2020ዓም

የሀገር ሰላምና የዜጎች ደህንነት ሊረጋገጥ የሚችለዉ ሁሉም ወገኖች ለሁለንተናዊ መፍትሄ ተግተዉ ስሰሩ ብቻ ነው
የሀገር ሰላምና የዜጎች ደህንነት ሊረጋገጥ የሚችለዉ ሁሉም ወገኖች ለሁለንተናዊ መፍትሄ ተግተዉ ስሰሩ ብቻ ነው

(የኦነግ መግለጫ – የካቲት 14, 2012)

የክስተቱን መንስዔና አጠቃላይ ምንነቱን አስመልክቶ እስካሁን በቂ ግንዛቤና መረጃ ባይኖረንም እንኳ በትናንትናዉ ዕለት (የካቲት 13, 2012) በቡራዩ ከተማ የተፈጸመዉንና የኮሚሽኔር ሰለሞን ታደሰ ሕይወት የጠፋበትን ግድያና የአካል ጉዳት ያደረሰዉን ጥቃት በጽኑ እናወግዛለን። በጠፋዉ ሕይወትና በደረሰዉ አካላዊ ጉዳት ለተጎዱትም የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለተጎጂ ቤተሰቦችና ጓደኞች ሁሉ መጽናናቱን እንመኛለን።

በእንዲህ መሰሉ ጥቃትም ይሁን በሌላ በምንም መልኩ የተወሰኑ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ዒላማ አድርጎ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና አላስፈላጊ ጫናዎች የሀገሪቱን ችግሮች ይበልጥ ያባብሱና ያወሳስቡ እንደሆነ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ ያመጣሉ ብለንም አናምንም። በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ መንገዶች እየታዩ ላሉት የፖለቲካና የደህንነት ችግሮች ሁሉ ሰላማዊና ዘላቂ መፍትሄ ለማፈላለግ መንግሥት ከፍተኛዉን ድርሻና ኃላፍነት እንዳለዉ ይታወቃል። የዚህች ሀገር የፖለቲካ ኃይሎች ሁሉም ይህንን አስመልክቶ የድርሻቸዉን ለመወጣት ግዴታ አለባቸዉ። ሰፊዉ ሕዝብም እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ሕዝብ የተጋረጡብንን ችግሮች በተመለከተ የችግሮቹን መንስዔና መፍትሄያቸዉን ለይቶ ያሉብን ችግሮች ለዘለቄታዉ መፍትሄ በሚያገኙበት አቅጣጫ ላይ የበኩሉን እገዛ ለማድረግ በንቃት መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነዉ ብለን እናምናለን።

ስለሆነም፣ ባሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ላይ አስፈሪና ዘግናኝ የሆነ የስጋት ደመናን አንዣቦ ያሉት የፖለቲካና የደህንነት ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ልያገኙ የሚችሉበትን መንገድ ለማፈላለግ ሁሉም ወገኖች ኃላፍነትና ግዴታቸዉን በላቀ የተጠያቂነት/responsibility መንፈስ እንዲወጡ ኦነግ አጥብቆ ይማጸናል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ መንግሥት የዜጎች ነፃነትና ደህንነት ልረጋገጥበት የሚችለዉ ሁለንተናዊ መፍትሄ ልገኝ የሚችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንደመንግሥት የተረከበዉን ታሪካዊ ኃላፍነትና ተጠያቂነት መወጣቱ የወሳኝነት ሚና እንዳለዉ ተገንዝቦ ይህንን ኃላፊነቱን በገንቢ ሁኔታ እንዲወጣ በአፅንዖት እናሳስባለን።

ድል ለሰፊዉ ሕዝብ !

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር

የካቲት 14, 2012