ስለ ዶክተር ዓብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒትር ሆኖ በመመረጡ ከአፋር ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲየወጣ መግልጫ


April 3, 2018
ስለ ዶክተር ዓብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒትር ሆኖ በመመረጡ ከአፋር ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲየወጣ መግልጫ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትህና እኩልነት የናፈቀው በመሆኑ በኣዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር መመረጥ ደስታውን እየገልጸ ይገኛል።
የኣፋር ነጻ አውጭ ግንባር ፓርቲ በዶክተር ዓብይ አህመድ መመረጥ የኢህአደግ የተለመደ ድራማ ወይስ ለወጥ ፈላጊ ድርጅቶች የህውሃት የበላይነት የመረራችው በአንድነት አዲሲቱን የአጋራ ኢትዮጵያን ሰላም የሰፈነባት ፍትህ የተረጋገጠባት የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የተከበረባት ሃገር ለማየት ባደረጉት ቁርተኝነት ከሆነ እሰየው እንላለን።
የተለመደው ድራማ ከሆነ በአሁኑ ሰአት የተነሳው የለውጥ ፈላጊ ትውልድ ትግል ለመግታት እና የእፎይታ ግዜ ለመውሰድ ታስቦ ከሆነ የለውጥ ፈላጊውን ትውልድ ትግል ማንም ሊገታው የማይችል አንድ ግዜ የተቀጣጠለ ሰደድ መሆኑን በመግለጽ በ አገሪቷ ለረጅም አመታት በጉጉት ይጠብቅ የነበረውን እውነተኛ የፌደራል ስርዓት እውን እይዲሆን እንጠይቃለን። ይህም ዕውን እንዲሆን ከ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲፈጸሙ የምንፈልጋቸውን ዋና ዋናና ወቅታዊ ጉዳዮች እንድሚከተለው እናቀርባለን።
የአስቸኳይ ጊዜ ኣዋጁን ማንሳት የፖሊቲካ፤ የሃይማኖትና የሰበዓዊ መብት ታጋዮችን ያለቅድመ ሁኔታ መፍታት ከተቃዋሚ የፖሊቲካ ሃይሎች ጋር ግልጽና እውነተኝነት በተሞላበት መንገድ የውይይት መድረክ መክፈት፤ እንዲሁም የፖሊቲካና የዲሞክራሲውን ምህዳር በማስፍት የመጻፍና የመሰብሰብ መብትን ማስከበር።
የፌደራል ፖሊስ፤ የሴኩሪቲና የመከላከያን የበላይነት ከክልሎች በማስወገድ፤ በነጻነት የራሳቸውን ክልል እንዲያስተዳድሩና የሕዝቦቻቸውን ጥያቄወች በዲሞክራሲያዊ መንግድ እንዲፈቱ ማድረግ።
በልማት ምክኒይት ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ እና በኣስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለተጎዱ የሞያሌና አካባቢዋ ኑዋሪውውች የመልሶ ማቋቋም ስራ እንዲስራ እንጥይቃለን።
የኣፋር ነጻ አውጭ ግንባር ፓርቲ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለኣገራችንና ለሕዝባችን አዲስ ሞእራፍ በመክፈት፤ በነጻ መድርክ ውይይትና ግልጽነት የተሞላበት መግባባት በምፍጠር፤ ውድ ኢትዮጵያችን አብረን መገንባት እንድንችል፤ እድገትና ብልጽግናዋን ለማስፋትና ለማሳደግ፤ ይህን መልካም አጋጣሚውን እንዲጠቀምበት እናሳስባለን።

የአፋር ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ