ኣግባብነት የሌለዉ መንገድ ወደ መፍትሔ ኣያመራንም

ኣግባብነት የሌለዉ መንገድ ወደ መፍትሔ ኣያመራንም

(የኦነግ መግለጫ – ታሕሳስ 25 2018)

addaበኦነግ፣ በኢትዮጵያ መንግስትና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መካከል ከተደረሱ ስምምነቶች ዉስጥ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ተግባራዊ በማድረጉ ሂደት ላይ የሚሰራ ኣንድ የጋራ ኮሚቴ ከኦነግና ከኦዴፓ በጋራ ተዋቅሮ በመስራት ላይ ይገኛል። ይህ ኮሚቴ ከሁለቱም ወገኖች (ከኦነግና ከኦዴፓ) 3, 3 ሰዎችን ያካተተ ነው። ኮሚቴዉ የተቋቋመዉ በኦነግ ሊቀ-መንበር በአቶ ዳዉድ ኢብሳና የኦዴፓ ምክትል ሊቀ-መንበር እንድሁም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት በሆኑት በዶ/ር ለማ መገርሳ ነው። እነዚህ ሁለቱ የበላይ አመራር በጋራ በመሆን የኮሚቴዉን ስራ በበላይነት ይከታተላሉ።

ይህ ኮሚቴ የተሰጠዉን ግዳጅ ስያጠናቅቅ ለኦነግ ሊቀ-መንበር ለኣቶ ዳዉድ ኢብሳና ለኦዴፓ ምክትል ሊቀ-መንበር ለዶ/ር ለማ መገርሳ የስራ ሪፖርቱን ያቀርባል። ሪፖርቱ የሚቀርብላቸዉ ሁለቱ የበላይ አመራርም በሚቀርብላቸዉ ሪፕርት ላይ በመመርኮዝ ተመካክሮ ተገቢዉን ዉሳኔ ይሰጡበታል። የዚህን ኮሚቴ የስራ ኣፈጻጸምና ዉጤት በተመለከተ ለሕዝቡ መረጃም ሆኔ ማብራሪያ መስጠት ትክክለኛ፣ ተገቢና ዉጤታማም የሚሆነው ከላይ የተገለጹትን የአሰራር ሂደትና ቅደም-ተከተሉን ጠብቆ ስራው ስጠናቀቅ ብቻ ነው።

ይህ ስራ ከላይ በተገለጸዉ መልኩ ተገቢዉን ሂደት ተከትሎ ከኣንድ እልባት ሳይደረስ በኣንድ ወገን ሐሳብ ላይ ብቻ ተንተርሶ ለሕዝቡ የሚቀርብ መግለጫም ሆነ ማብራሪያ የተሟላ፣ ዉጤታማና ተገቢም ልሆን ኣይችልም። ስለሆነም የጋራ ኮሚቴዉ ኣባል የሆኑትን ኣቶ ሞገስ ኢዳኤን ብቻ ዋቢ በማድረግ ይህን ጉዳይ የሚመለከቱ ዘገባዎች በዛሬዉ ዕለት በተለያዩ የዜና ኣዉታሮች መሰራጨታቸዉ ተቀባይነት የሌለዉና ኣግባብነት የሌለው ኣካሄድ መሆኑን እናስገነዝባለን።

ድል ለኦሮሞ ሕዝብ !

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
ታሕሳስ 25 2018